በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ጉዳ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለክፍለ ከተማ ውሃ እና ማዕድን ኢነርጅ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተፈጨ ድንጋይ ባለ 01 የካሬ ሜትር ብዛት 21,845ሜ3 እና ከዚያ በላይ የመሆን እንዲሁም ባለ 00 የካሬ ሜትር ብዛት በ112ሜ3 እና ከዚያ በላይ የሆነውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ፡፡
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ጉዳ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለክፍለ ከተማ ውሃ እና ማዕድን ኢነርጅ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተፈጨ ድንጋይ ባለ 01 የካሬ ሜትር ብዛት 21,845ሜ3 እና ከዚያ በላይ የመሆን እንዲሁም ባለ 00 የካሬ ሜትር ብዛት በ112ሜ3 እና ከዚያ በላይ የሆነውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ፡፡
ስለዚህ በግልጽ ጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቶች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቶች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የ1ሜ3 የተፈጨ ድንጋይ (ጠጠርን) የምትገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ዋጋ ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ተጫራቶች የሚገዙበትን ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 2000.00 ብር ሲንቄ አካውንት ቁጥር 1054490110216 በማስገባት ክፍለ ከተማ ገቢዎች በመሄድ ወደ ደረሰኝ በማስቀየር የጨረታ ሰነድ ከከፍለ ከተማው ፋይናንስ መውሰድ ትችላላችሁ።
- ለሽያጭ የቀረበው ማዕድን የሚገኘው በገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ለኩሌ ጌጃ ወረዳ ልዩ ሰሙ ቦነያ የሚባል። ከአለምገና ወደ ቡታጅራ በሚወስደው መንገድ 10 ኪሎ ሜትር ሲሆን ከቡታጅራ አስፓልት 500 ሜትር ገባ ብሎ የሚገኝ ስለሆነ በአካል በመጎብኘት የሚገዙበትን ዋጋ መሙላት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ማዕድኑን ለመግዛት ያሸነፉትን ገንዘብ በ10 ቀን ውስጥ መ/ቤቱ ባዘጋጀው ባንከ ገቢ በማድረግ ያሸነፈውን ማዕድን ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ማንሳት የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ብር 300,000.00(ሶስት መቶ ሺህ ብር) በሲፒአ ወይም በሁኔታ የማይገደብ የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ብቻ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ተከታታይ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን በ4፡30 የሚከፈት ሆኖ ተጫራቾች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ከላይ የተገለጸው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል፣፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912078675/0911551369 መጠየቅ ይችላሉ ::
በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ጉዳ ክፍለ
ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
