የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ማስተማር ስራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 01 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ ፤ ሎት 02 የላብራቶሪ ዕቃዎችና ኬሚካሎች ግዥ፣ ሎት 03 የህክምና ዕቃዎችና ሬጀንቶች ግዥ፣ ሎት 04 የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ ግዥ፣ ሎት 05 የደንብ ልብስ ግዥ፣ ሎት 06 የህንፃ መሳሪዎች ግዥ፣ ሎት 07 የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ የላብራቶሪ እቃዎች ግዥ፣ ሎት 08 የመሬት አስተዳደር እና የቅየሳ እቃዎች ግዥ ፣ሎት 09 ፍራሽና ትራስ ግዥ፣ ሎት 10 የፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ፣ ሎት 11 የቤተ ሙከራ ኢፖከሲ (Epoxy) ግዥ ሎት 12 የኒሮ ሰርጅን ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Injibara University (የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 04/2017
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ማስተማር ስራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 01 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ ፤ ሎት 02 የላብራቶሪ ዕቃዎችና ኬሚካሎች ግዥ፣ ሎት 03 የህክምና ዕቃዎችና ሬጀንቶች ግዥ፣ ሎት 04 የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ ግዥ፣ ሎት 05 የደንብ ልብስ ግዥ፣ ሎት 06 የህንፃ መሳሪዎች ግዥ፣ ሎት 07 የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ የላብራቶሪ እቃዎች ግዥ፣ ሎት 08 የመሬት አስተዳደር እና የቅየሳ እቃዎች ግዥ ፣ሎት 09 ፍራሽና ትራስ ግዥ፣ ሎት 10 የፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ፣ ሎት 11 የቤተ ሙከራ ኢፖከሲ (Epoxy) ግዥ ሎት 12 የኒሮ ሰርጅን ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
- አድራሻ በአማራ ብሔራዊ ክልልዊ መንግስት በአዊ አስ/ዞን እንጅባራ ከተማ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ነው።
- በጨረታ መወዳደር የሚችሉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ ብቻ ናቸው ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት በኢትዮጵያ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ከፍሎ በዩኒቨርሲቲው ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 110 በመግዛት እቃው የሚሸጥበትን ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ የድርጅቱን ስምና ማህተም በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለይቶ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ግዥ ስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 110 ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ሎት 01 የኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎች ግዥ 300,000.00 ሎት 02 የላብራቶሪ ዕቃዎችና ኬሚካሎች ግዥ 300,000.00 ሎት 03 የህክምና እቃዎችና ሬጀንቶች ግዥ 300,000.00፣ ሎት 04 የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ ግዥ 200,000.00፣ ሎት 05 የደንብ ልብስ ግዥ 50,000 ሎት 06 የህንፃ መሳሪዎች ግዥ 100,000.00፤ ሎት 07 የኤሌከትሪካል ኢንጂነሪንግ ግዥ 200.000.00፣ ሎት 08 የመሬት አስተዳደር እና የቅየሳ እቃዎች ግዥ 200,000.00፣ ሎት 09 ፍራሽና ትራስ ግዥ 200,000.00፣ ሎት 10 የፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ 200,000፣ ሎት 11 የቤተ ሙከራ ኢፖከሲ (Epoxy) ግዥ 100,000.00)፣ ሎት 12 የኒሮ ሰርጅን ዕቃዎች ግዥ 100,000.00 በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ተመዝጋቢ ከሆኑ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው:: የሚገዛው ዕቃ ከ200,000.00/ ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ የሚሆን ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች ብቻ የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ ገንዘብ 10% በጥሬ ገንዘብ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፋቸውን እቃዎች ዩኒቨርሲቲው ግቢ ድረስ በራሳቸው ወጭ በማቅረብ ማስረከብ አለባቸው ::
- የጨረታ ሰነዱ ማስገባት የሚጀምረው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታው በ16 ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጎ በ4:30 ይከፈታል የጨረታ መክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ሰዓት አቅራቢዎች ወይም ወኪሎች ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዥ ይሆናሉ ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ7 ሰባት ቀን በኋላ ባሎት 8 ቀን ውስጥ ውል መያዝ አለባቸው።
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- ዩኒቨርሲቲው ባወጣው ጨረታ ላይ 20% የመቀነስ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው ::
- ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 0588270621 ወይም በአካል ዩኒቨርሲቲው ድረስ በመምጣት መጠየቅ ይቻላል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ሎት 08 የመሬት አስተዳደር እና የቅየሳ እቃዎች ግዥ ቴከኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ኮፒና አርጂናል ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
