Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111170171
  • Website
  • Deadline18 Nov 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ 1ኛ/የጽ/መሳሪያ 20.000 ብር 2ኛ/ የፕሪንተር ቀለም 10.000 ብር 3ኛ/የጽዳት ዕቃዎች 800 ብር 4ኛ/የተለያዩ ቋሚ የቢሮ እቃዎች 1000 ብር 5ኛ/ የእንሰሳት መድሃኒት 10.000 ብር 6ኛ/ የኤሌክትሮኒክ እቃዎች 10.000 ብር 7ኛ/ ደረቅ ጭነት 2000 ብር 8ኛ/ የስፖርት ትጥቅና ማቴሪያሎች 6000 ብር 9ኛ/የደንብ ልብስ የተዘጋጁ 8000 ብር 10/ደንብ ልብስ ጫማዎች 10.000 ብር 11ኛ ደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ 6000 ብር 12ኛ/ፈርኒቸር 3000 ብር 13ኛ/የደን ዛፍ ዘር 2000 ብር 14ኛ/ህትመት 1000 ብር 15ኛ/ የመኪና እቃ መለዋወጫ 3000 ብር 16/የመኪና ጎማና ከለማዳሪ 2000 ብር በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም:-

የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር ከብር 200.000/ ሁለት መቶ ሺህ ብር /በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረዉ የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተው ኮፒና ኦርጅናል ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ተሞልቶ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በተዘረዘረው ሎት የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚስጥ ሲ.ፒ.ኦ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር አፍ ክሬዲት ወይም በገቢ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቹ በዋጋ መሙሊያ ሰነድ ላይ ስም ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጫረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን 3፡30 ድረስ በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጫረታ በተዘጋጀ ሳጥኑ ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ዕቃውን በሚ/ወ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች ባለት ንብረት ክፍል ውስጥ ማድረስ ይኖርባቸዋል።
  7. የጨረታ ውድድሩ እንደአስፈላጊነቱ በነጠላ ዋጋ ወይም በሎት ሊሆን ይችላል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች በአካል ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ላይ የጨረታ ሰነድ የመጨረሻ ማስገቢያ ከጠዋቱ 3:30 ሆኖ ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  9. ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን የደንብ ልብስ የተዘጋጁ፣ የደንብ ልብስ ጫማዎች እና የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ ጥራት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ ናሙና ሳምፕል ተጫራቹ ያቀርባል የስፖርት ትጥቅና ማቴሪያሎች ጥራት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ ናሙና ሳምፕል/ መ/ቤቱ ያቀርባል ተጫራቾች በተጨማሪ ለፕሪንተር ቀለም ከአምራቹ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ስ/ቁ 0111170171 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender