በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኸምራ ዞን የጋዝጊቢላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ከጋዝጊብላ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን ማለትም በምድብ 1 ፅዳት እቃዎች በምድብ 2 የግንባታ እቃዎች በምድብ 3. የውሃ እቃዎች በምድብ 4. የስፓርት እቃዎች እና በምድብ 5. ጣውላና ኮፒስታቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ር ቡድን
በድጋሚ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኸምራ ዞን የጋዝጊቢላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ከጋዝጊብላ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን ማለትም በምድብ 1 ፅዳት እቃዎች በምድብ 2 የግንባታ እቃዎች በምድብ 3. የውሃ እቃዎች በምድብ 4. የስፓርት እቃዎች እና በምድብ 5. ጣውላና ኮፒስታቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በየዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር እና ከዛ በላይ ከሆነ የተጨማሪ አሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዛት ሲወጡ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ መያዝ አለባቸው።
- የሚገዙትን እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች በየምድቡ የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ/ በመክፈል በጋዝጊብላ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት በሳጥን ማግኘት ይቻላል:: የጨረታ ሰነዱን በሥራ ሰዓት ብቻ መግዛት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በሚወዳደሩበት ምድብ ከጠቅላላ ዋጋ (ቫትን ጨምሮ) 1 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ካይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እንዲሁም ከመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ በመሂ አንድ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ዋናውን ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በፖስታ አሽገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ለሚፈልጉ በፖስታ አስገብተው የጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ኮፒ በማለት እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት የሚቻል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:31 ይታሸግና በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰባት ይከፈታል ይሁን እንጅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጽ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው።
- የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም በፍሉድ የተሰረዘ ካለው ሰነዱ ተቀባይነት የለውም፡፡
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋል።
- መ/ቤቱ በየምድቡ ያሉት የእቃዎቹ የጨረታ ሰነዶች በሎት ወይም በነጠላ ዋጋ የምናወዳድር ይሆናል
- የጨረታው አሸናፊ እቃውን በራሱ ትራንስፖርት ጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት፤ ከታዘዘው እስፔስፊኬሽን ውጭ እቃ ቢያቀርብ በራሱ ወጪ እቃውን ወስዶ ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የእቃ ዋጋ ሲሞሉ እስፔስፌክሽን የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች የእቃውን መለያና እስፔስፌክሽን መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን እስፔስፍኬሽን እና መለያ የማይሞላ ተጫራች ሰነዱ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው 1ኛ የወጣው ተጫራች ውል እስኪወስድ ድረስ 1ኛ ና 2ኛ የወጡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስላቸውም፡፡ ሌሎቹ ተወዳዳሪዎች ግን አሸናፊው ከተለየ በኋላ ወዲያውኑ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት የውለታ ማስከበሪያ ይዞ በመቅረብ ውለታ መውሰድ ይኖርበታል።
- ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ካላንደር (ዝግ ከሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ጽ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ የግዥ መጠኑን 20% ከፍና ዝቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግን አስር ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመገኘት ወይም በሞባይል ስልከ ቁጥር 09 21 26 4853 ወይም 09 21 19 21 27 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
የጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ር ቡድን
