Tender Detail

Tender Details

  • Deadline07 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፎ የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች 8/02/2017 ዓ.ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፤


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፎ የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች 8/02/2017 ዓ.ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፤ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በመግዛትና ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት ከታች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች:-

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደስ የንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንስ (Clerance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታከስ ማዕከል ያሳውቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር እያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት አስከ ቀን 28/02/07 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 ሰዓት እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከ ረፋዳ 5፡00 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታው ሰነድ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገቢ አሰባሰብ ቢሮ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ
  3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100.000 (አንድ መቶ ሺህ ብር በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡

ተ.ቁ

የጨረታ ቦታ

የጨረታው ዓይነት

ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች

የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አዋሽ ጉ/ቅ/ፅ/ጽ/ቤት

ግልፅ ጨረታና ሐራጅ

ጫማዎች አልባሳት ኮስሞቲክስ የመኪና መለዋወጫ፤ ኤሌክትሮኒክስ፤ የስፓርት እቃዎች፤ የሞባይል ቀፎ፤ ምግብ ነክ ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች

ለግልጽ ጨረታ በ28/02/2017 እስከ ጠዋት 3፡45፤ ከሐራጅ ጨረታ እስከ 4፡45

ለግልጽ ጨረታ በ28/02/2017 እስከ ጠዋት 4፡00፤ ለሐራጅ ጨረታ እስከ 5፡00

  1. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (አስኬጁል መሰረት በአዋሸጉ/ት/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታው መከፈቻ ቦታ በአዋሽ ገ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለቤት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
  3. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታዉ ዋስትና ያስያዙት (CPO ) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  4. ከአሽናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
  5. ከላይ በተ ቁ7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የክፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  6. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር- 022-224 1402 ደውለው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይቻላል።

 

በኢትዮጵያ  ፌዴራላዊ  ዲሞክራሲያዊ  ሪፐብሊክ  በጉምሩክ  ኮሚሽን  አዋሽ  ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender