በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከ/ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ለውጊያ ምህንድስና ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፣ግ/ጨ/002/2017ዓ.ም
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከ/ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ለውጊያ ምህንድስና ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፦
- የተለያዩ የቢሮ የፅህፈት እና የትምህርት መርጃ ዕቃዎች
- የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች
- የተለያዩ የእጅ መገልገያ ዕቃዎች
- የተለያዩ የቤት ጥገና ዕቃዎች
- የተለያዩ የህሙማን ቀለብ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዚህ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች አግባብ ያለው የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የቫት ሰርተፍኬት ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ፣ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ግብር ስለመከፈላቸው ወይም ጨረታ እንዲሳተፉ የተሰጠ ደብዳቤ ወይም ወርሃዊ የቫት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉና የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት አ/አ እንጦጦ ከሚገኘው የውጊያ ምህንድስና ኮሌጅ ግቢ ፋይናንስ ቢሮ በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፣ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ C.P.O በሚጫረቱበት የዕቃ ዓይነት ከታች በተገለፀው የገንዘብ መጠን ማሰራት ይጠበቅባቸዋል፣ የተለያዩ የቢሮ የፅህፈት እና የትምህርት መርጃ ዕቃዎች=12,000.00 የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች= 8,400.00 የተለያዩ የእጅ መገልገያ ዕቃዎች =4,000.00 ፤ የተለያዩ የቤት ጥገና ዕቃዎች= 30,000.00 የተለያዩ የህሙማን ቀለብ= 3,200.00 በመያዝ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፣ ጨረታው ሐሙስ ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እንጦጦ በሚገኘው በውጊያ ምህንድስና ኮሌጅ ቅጥር ግቢ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣፣
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር፡ -0967169078-0929413951
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከ/ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ
የውጊያ ምህንድስና ኮሌጅ
