የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት ለ 2017 ዓ.ም የስራ ዘመን ከዚህ በታች በጥቅል ስም የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት ለ 2017 ዓ.ም የስራ ዘመን ከዚህ በታች በጥቅል ስም የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
-
- የጽህፈት መሳሪያዎችን
- የፋብሪካ ዕቃዎች
- የፅዳት ዕቃዎች
- የመብራት ዕቃዎችና
- የልማት ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች
-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ ቁጥር (TIN No) የተሰጣቸው መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ። እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ 2% በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር በሰም በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 100.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሳጥን በ11ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዕቃ ሞዴል ወይም አይነት በጨረታው ሰነድ ላይ በግልጽ መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከመንግስት ግዢ ያልታገደ መሆን አለበት፡፡
- በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ያሳግዳል፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ሰአት ከላይ የተጠቀሱትን አስፈላጊ መረጃዎች አሟልተው ያልተገኙ ተወዳዳሪዎች ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ፡፡
- አሸናፊው ያሸነፈውን እቃ በራሱ ወጪ አጓጉዞ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት አቅርቦ ማስረከብ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 046-3350901 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
የቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት
