በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በየካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የኮተቤ ጤና ጣቢያ
የመጀመሪያ ዙር ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2017
በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች በሎት የተገለፁ እቃዎችን በጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. የደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ብር 8000 (ስምንት ሺህ ብር)
- ሎት 2 የጽዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 6000 (ስድስት ሺህ ብር)
- ሎት 3 የጽህፈት መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 4 የኮምፒውተርና ኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 7000 (ሰባት ሺህ ብር)
- ሎት 5 የመኪና እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 3000 (ሶስት ሺህ ብር
- ሎት 6 የጥገና እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 2000 (ሁለት ሺህ ብር)
- ሎት 7 የቧንባ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 3000 (ሶስት ሺህ ብር)
- ሎት 8 የልብስ ማጠቢያ ማሽን የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 10000 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት 9 ቋሚ የፈርኒቸር እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 4000 (አራት ሺህ ብር)
- ሎት 10 የኤሌክትሪክ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 4000 (አራት ሺህ ብር)
- ሎት 11 የሕትመቶች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 6000 (ስድስት ሺህ ብር)
- ሎት 12 መድሃኒቶች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 13 ቋሚ የህክምና መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 14 የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች ጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 15 የደንብ ልብስ ስፌት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 7000 (ሰባት ሺህ ብር) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
2. የግብር መክፈል ግዴታዎችን የተወጡ መሆኑን የሚገልፅ ከግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
3. ጨረታውን የሚወዳደሩት በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ መሆን አለበት፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር በየሎት ላይ በተዘረዘረው መሰረት ማስያዝ ይኖርበታል። የጨረታ ሰነዱን ሲያስገባ (በcpo) ብቻ በጤና ጣቢያ ስም አሰርቶ ማስያዝ ይኖርበታል።
5. የጨረታ ማስከበሪያ(በc.p.o) የስያዙት ብር ለተሸነፉ ድርጅቶች ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
6. ጨረታውን ለአሸነፉ ድርጅቶች ደግሞ የጨረታውን ውል ማስከበሪያ ብር 10% አስይዘው እንደተፈራረሙ በጨረታ ማስያዣ የተያዘው ብር ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ በየሎቱ በማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር የስራ ቀናት ውስጥ) ዘወትር በስራ ሰዓት ኮተቤ ጤና ጣቢያ 4ኛ ቢሮ ቁጥር 55 ግዥ ክፍል በአካል ቀርቦ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
8.ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውን፤ አድራሻ ፤ ፊርማ እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
9. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ መሰረት በማድረግ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት አንድ ኮፒ እና ኦርጅናል አሽገው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 54 በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በአስራ አንደኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ (ሶስት ሰዓት ተኩል) ላይ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
12. ጤና ጣቢያ የሚገዛቸውን እቃዎች 20% የመጨመር እና የመቀነስ መብት አለው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 091 105 2054. 092 183 0596 እና 011 646 22973 ደውለው ይጠይቁ
አድራሻ ኮተቤ ጤና ጣቢያ ከ02 ወደታች በሚወስደው መንገድ 600 ሜትር ገባ ብሎ ነው፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ የኮተቤ ጤና ጣቢያ
