Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክፍለ ከተማ በወረዳ 7 ስር የሚገኘው የሜ/ጀ ኃየሎም አርአያ የመጀ/ደ/ት/ቤት
  • Address ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ ኖከ ማደያ ጎላ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ገባ ብሎ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-15-40-84
  • Website
  • Deadline09 Nov 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክፍለ ከተማ በወረዳ 7 ስር የሚገኘው የሜ/ጀ ኃየሎም አርአያ የመጀ/ደ/ት/ቤት


ግልፅ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  መለያ  ቁጥር 001

በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክፍለ ከተማ በወረዳ 7 ስር የሚገኘው የሜ/ጀ ኃየሎም አርአያ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት:-

ሎት1 - አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 2,000፣

ሎት 2 - አላቂ የትምህርት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 2,000

ሎት 3 - የሰራተኞች የደንብ ልብሶች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 2,500

ሎት 4 - አላቂ የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 2.000፣

ሎት 5 - አሌክትሮኒክስ እቃዎች ማስከበሪያ በብር መጠን 3,000፣

ሎት 6 - ቋሚ የቢሮ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 2,000፣

ሎት 7 - የላብራቶሪ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 1,000፣

ሎት 8 - የህትመት ስራዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 2.000፤

ሎት 9 - የስፖርት ትጥቅ የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 3,000፣

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር አጠናቃችሁ የከፈሉ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ-ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ የተመዘገቡ የቫትና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑና የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. ለጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሜ/ጀ/ ኃየሎም አርአያ የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት በግንባር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የምትጫረቱትን እቃዎች ሳምፕል የሚቀርብባቸው ለሎት 1፣ ለሎት 2፣ ለሎት 3፣ ለሎት 4፣ ለሎት 5፣ ለሎት 8 እና ለሎት 9 ናሙናውን ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን በፊት ሳምፕል በሚቀርብባቸው ሎቶች ላይ ያላቀረቡ ለጨረታ ውድድር አይቀርቡም ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታ የማናሳትፍ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
  6. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ስርዝ ድልዝ የሆነ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፋባቸውን ዕቃዎች በራሱ / ባሸናፊው) ትራንስፖርት ከነጉልበት ክፍያው ግዢ ፈፃሚው መ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች የምታቀርቡትን ዋጋ ዝርዝር በሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በግልፅ ሞልታችሁ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውንና ኮፒ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 1ኛው ቀን ድረስ በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን በሜ/ጄ/ኃየሎም አርአያ የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
  9. የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሜ/ጀ/ኃየሎም አርአያ የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ 10ኛው ቀን የበዓል ቀን ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ማሳሰቢያ ፡- ከእስፔስፊኬሽን እና ከዋጋ ማቅረቢያ ውጭ ሁለት ዋጋ መሙላት አይቻልም፤ እንዲሁም በራስ በተሰጠው ሎት ፎርም ውጭ በእስከርቢቶ መሙላት እና ከታች አማራጭ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

አድራሻ ፡- ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ ኖከ ማደያ ጎላ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር :- 011-5-15-40-84/09-66-52-10-10

ፖስታ ሳጥን ፡- 25993/1000

የሜ/ጀ/ኃየሎም አርአያ የመጀ/ደ/ት/ቤት

 

Save Tender