የአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ፍርድ ቤት የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የሟች ደበበ ገ/ ጻዲቅ ንብረት የሆነው ቤትና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ አስቧል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሣሾች እነ ህጻን ሳሙኤል ነጋሽ (9 ሰዎች) እና በአፈ/ተከሣሽ ንጉሴ ገ/ጻዲቅ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የሟች ደበበ ገ/ ጻዲቅ ንብረት የሆነው ቤትና ቦታ በሰላ ድንጋይ ከተማ 01 ቀበሌ ጻድቃኔ ጎጥ በምስራቅ ዘበነ ንጋቱ፣ በምዕራብ ሸዋበረ፣ በሰሜን ግዛው ወንድምህን እና በደቡብ መንገድ አዋሣኝ የሚገኘው 250 ካ/ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው በብር 1,250,310.45 /አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሣ ሺህ ሶስት መቶ አስር ብር ከአርባ አምስት ሣንቲም/ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ ህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
በመሆኑም:-
- ገዥው /ተጫራቹ/ ያሸነፈበትን ¼ኛ ገንዘብ ወዲያውኑ ለሐራጅ ባዩ የማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡
- ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው ለፍርድ ማስፈፀሚያ ነው፡፡
- ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል፡፡ በፍ/ሥ/ ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሐራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡
- የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል፡፡
የሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
