የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ኦዲተር መ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-01/2017
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1፡- ኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች፣
ሎት 2፡- የቢሮ ጽሕፈት መሣሪያዎችንና አላቂ ዕቃዎችን፣
ሎት 3፡- የጽዳት ዕቃዎች፣
ሎት 4፡- ፈርኒቸር (ቋሚ የቢሮ) ዕቃዎች እና
ሎት 5፡- የደንብ ልብስ
በዚሁ መሰረት ከላይ ለተጠቀሱ ዕቃዎች በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች:-
- የታደሰ የዘርፋ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ ዕሴት ታከስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት እና የዕቃ አቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ያልታገደ የንግድ ፈቃድ ወይም ታግዶ የነበረ ከሆነ የእገዳ ጊዜውን ስለመጨረሱ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመ/ቤቱ ግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙብት በቢሮው 1ኛ ፎቅ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ ቢሮ ቁጥር 113 ይከፈታል፡፡ ሆኖም 16ኛው ቀን የሥራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለመወዳደሩት ዕቃዎች ከሚያቀርቡት ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በእራሳቸው ፈቃድ በጊዜው አለመገኘት የጨረታ ሳጥኑን ከመክፈት እያስተጓጉልም፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች በውሉ መሰረት ግዥ የሚፈጸምባቸውን ዕቃዎች እስከ መ/ቤቱ ድረስ በራሳቸው ወጪ አቅርበው ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በክፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የመ/ቤቱ አድራሻ፦ በሀዋሳ ከተማ ሲዳማ ባንከ ዋናው ቢሮ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046-2-12-71-38
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ኦዲተር መ/ቤት
