የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ GC/BC-4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአዲስ አባባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የካርጎ አገልግሎት ግቢ ውስጥ የኮንፈረንስ፣ የመቀየሪያ ክፍል፣ የሴፕቲክ ታንክ እና የስፖርት ሜዳ ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T-500
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ GC/BC-4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአዲስ አባባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የካርጎ አገልግሎት ግቢ ውስጥ የኮንፈረንስ፣ የመቀየሪያ ክፍል፣ የሴፕቲክ ታንክ እና የስፖርት ሜዳ ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች የ2016 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው እንዲሁም የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 (E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የጨረታ ቁጥር SSNT-T500 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢ-ሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/ ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ከባንከ የሚቀርብ ሁኔታዊ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ግቢ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ 9፡15 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡ - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ወ/ሮ ሰላማዊት አባተ
ስልክ ቁጥር፡- 011-5-17-42-58
ኢ-ሜይል:- selamawita@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
