Tender Detail

Tender Details

  • Company በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ቃሊቲ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ግቢ ውስጥ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-22-45-04-40
  • Website
  • Deadline08 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

ለአሽ/ተሽ/ፈ/ቃ/ቁ/ባለስልጣን አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት


የጨረታ  ማስታወቂያ  ቁጥር 01/2017 ዓ.ም

ለአሽ/ተሽ/ፈ/ቃ/ቁ/ባለስልጣን አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎች ማለትም፤

ሎት 1 የደንብ ልብስ፣

ሎት 2 አላቂ የጽህፈት ዕቃዎች፣

ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች

ሎት 4 የህትመት ዕቃዎች

ሎት 5 ቋሚ የጽህፈት ዕቃዎች፣

ሎት 6 አላቂ የጽህፈት ዕቃዎች፣

ሎት 7 የተሽከርካሪ ዕቃዎች

ሎት 8 የቢሮ ቁሳቁስና ተገጣጣሚዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በመስኩ የተሰማሩ ህጋዊ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የኢፌዴሪ የገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተ.እ.ታ ተመዝጋቢዎች ለመሆናቸው ኮፒ ማስረጃ እና /Tin No/ ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 -10:00 ሰአትና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 39 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ /financial/ ሰነድ፣እንዲሁም አስፈላጊ ቴክኒካል ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በመለየት ኦርጂናልና ኮፒውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 31 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን በሎት 1,000 /አንድ ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ / CPO/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ በሰጣቸው ሰነድ ላይ መሙላት እና በእያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ፊርማ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና እንዲያቀርብ ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታ ከመክፈቻ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት ላይ ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ውሉን ሲዋዋሉ ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 10 70 49 72/09 22 45 04 40 ደውሎ መጠየቅ ወይም ቃሊቲ ማሰልጠኛ ግቢ ውስጥ ከሚገኘው ቅ/ጽ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 31 በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender