በሸገር ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የቡራዩ ከተማ ከፍተኛ ቅርንጫፍ የፅዳት እና የእስቴሽነሪ እቃዎች Lot 1፤ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች (Office Furniture) Lot 2 እና የሠራተኞች ደንብ ልብስ (Uniform and protections) Lot 3 በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በሸገር ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የቡራዩ ከተማ ከፍተኛ ቅርንጫፍ
የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የቡራዩ ከተማ ከፍተኛ ቅርንጫፍ
- የፅዳት እና የእስቴሽነሪ እቃዎች Lot 1
- ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች (Office Furniture) Lot 2
- የሠራተኞች ደንብ ልብስ (Uniform and protections) Lot 3 በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ተጫራቾች በድርጅቱ ጽ/ቤት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን ፤ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች -
- ተጫራቶች በዘርፉ የተደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ በስማቸው ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ :: የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በግልፅ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ለእየንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ 1000 ብር (አንድ ሺህ) በመክፈል ከድርጅቱ ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመምጣት ለጨረታ የተዘጋጀ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው እንዲሁም በፌዴራል ገ/ኢ/ ትብብር ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገ/ ኢ/ ትብብር ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ 30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ (ዋስትና (10%) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት የቴከኒከና የፋይናንስ ኦርጂናል እና በኮፒ ሁለት ሁለት በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 16ኛው ቀናት ሲሆን ቀጥሎ የሚውለው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት አድራሻ በሸገር ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የቡራዩ ከተማ ከፍተኛ ቅርንጫፍ ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251911798879 Office tel- +251911532249
በሸገር ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የቡራዩ ከተማ ከፍተኛ ቅርንጫፍ
