የጋምቤላ ሕ/ብ/ከ/መንግስት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መ/የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- መ/ቆ/አ/ቢ/03/2017
የጋምቤላ ሕ/ብ/ከ/መንግስት የመስኖና ቆላማ አከባቢ ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ገዝታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፡፡
ሎት 1፡- የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች (ላፕቶፕ፣ ፎቶ ኮፒ፣ ፕሪንተር… ወዘተ)፣
ሎት 2፡- የፈርኒቸር ዕቃዎች፣
ሎት 3- ለመስኖ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች (ቶታል ስቴሽን፣ ሌበሊንግ፣ ጀፕኤስ)፣
ሎት 4፡- የውሃ መሳቢያ ፓምፕ፣
ሎት 5፡- ጀነሬተር፣
በዚህም መሠረት ጨረታውን ስመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡-
- ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በመ/ቤቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በቢሮ ቁጥር 01 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸውና የዘመኑን እንቅስቃሴ የሚያመለከት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የአቅራቢነት የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ወይም በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ለሚጫረቱበት ዋጋ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ የሚሰጡት ዋጋ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘው የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሠነድ ማስገቢያ ሳጥን በ15ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሯችን ቅጥር ግቢ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው ሠነድ ማስገቢያ ቦታ በክልሉ መስኖ እና ቆላማ አከባቢ ቢሮ፤ ቢሮ ቁጥር 01 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት መስሪያ ቤታችን ድረስ በማቅረብ መገጣጠም ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ አስከ 20 ፐርሰንት የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ቢሯችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 047-5-51-12-08 ይጠቀሙ::
የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መ/የመስኖ
እና ቆላማ አካባቢ ቢሮ
