Tender Detail

Tender Details

  • Deadline05 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፤ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ማሸነሪዎች (ASPHALTPAVER MACHINE CRAWLER CRANE MACHINE CEMENT SILO MACHINE CRAWLER ASPHALT PAVER MACHINE STATIC ROLLER MA- CHINE) በግልጽ ጨረታ እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ሞባይሎች፤ የሞባይል ክፍሎች፣  የኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅና በሐራጅ ባሉበት ሁኔታ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች እና ልዩ ልዩ ዕቃዎች  ሽያጭ  ማስታወቂያ  ቁጥር 14/2017

 

አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፤ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ማሸነሪዎች (ASPHALTPAVER MACHINE CRAWLER CRANE MACHINE CEMENT SILO MACHINE CRAWLER ASPHALT PAVER MACHINE STATIC ROLLER MA- CHINE) በግልጽ ጨረታ እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ሞባይሎች፤ የሞባይል ክፍሎች፣  የኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅና በሐራጅ ባሉበት ሁኔታ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሐሙስ ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በመሆኑም፡-

  1. በመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች ግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች የመንገድ ግንባታ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።
  2. በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼከ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር እያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ደግሞ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል።
  3. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።
  4. ተጫራቾች የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች እና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. በዕቃና የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ወይም ማሽነሪዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼh (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሠርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) ማስያዝ እንደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እየገለጽን በተ.ቁ 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ የጨረታ ማስከበሪያ ቼh (CPO) ማስያዝ አለበት።
  7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነዱ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አ.አ.ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት

የዕቃ ሐራጅ

እስከ 25/02/2017

26/02/2017 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

የዕቃ ግልጽ

እስከ 26/02/2017

27/02/2017 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች ግልጽ ጨረታ

እስከ 27/02/2017

28/02/2017 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- አ.አ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
  2. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  3. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።
  4. ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ዉስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  5. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ - 011 - 470 - 85- 03

አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

 

አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender