Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ዋና መ/ቤት መሰረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ
  • Address ቄራ ፔፕስ ፊት ለፊት ጎቫን ህንፃ 2ኛ ፎቅ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 557 66 84
  • Website
  • Deadline12 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ዋና መ/ቤት ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን እና አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን በሽያጭ ለማስወገድ ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ዋና መ/ቤት መሰረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ


ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ዋና መ/ቤት ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን እና አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን በሽያጭ ለማስወገድ ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ዋና መ/ቤት ቄራ ፔፕስ ፊት ለፊት ጎቫን ህንፃ 2ኛ ፎቅ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ ቢሮ በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ዋና መ/ቤት ስም በተከፈተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000036194514 ከፍለው የባንከ ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚገዙትን ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ዋና መ/ቤት ቄራ ፔፕስ ፊት ለፊት ጎቫን ህንፃ 2ኛ ፎቅ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ንብረቶቹ በሚገኙበት ልደታ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ ዳማ ሀውስ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 701 ከፍል በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ ያገለገሉ የተገለፁትን አሟልቶ መገኘት ነው::
  7. ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች የመነሻ ዋጋ 10 በመቶ /10%/ ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
  8. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵየ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎት ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  9. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት፤ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋል ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም።
  10. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፤ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
  11. አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡ 
  12. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
  13. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011 557 66 84 / 09 18 28 07 94 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  14. የዕቃው መለኪያ በኪሎ የተገለጸው በግምት ስለሆነ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  15. አገልግሎቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ዋና መ/ቤት

መሰረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ

Save Tender