በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ ለ2017 ዓ.ም አገልግሎት የሚውል ቋሚ እቃዎች አላቂ እቃዎች ለህጻናት ማቆያ የሚያስፈልጉ እቃዎች የፅህፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት ዕቃዎች፤ የህክምና ዕቃዎች፤ አላቂ ሕክምና እቃዎች፣ መድሃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶት፤ የደንብ ልብስ፣ ዴስክቶፕ እና ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተር፣ ህትመት የሰራተኞች ሰዓት መቆጣጠሪያ ማሽን ከነዝርጋታው የአምቡላንስ ጂፒ ኤስ ከነመግጠሙ ዩፒ ኤስ የመስኮትና በሮች ጥገና የህንጻ ፍሳሽ ማስወገጃ ፒቪሲ ጥገና፣ የሻወር ቤት ጥገና፣ የሎከር ጥግና የመብራት ጥገናና ዝርጋታ፣ የቀለም ቅብ እና የፓርትሽን ስራ የAPTS ሼልፍ ከነ ዴስፕለይ የAshi pit ግንባታ የህክምና እቃዎች ካሊብሬሽን እና የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ ለ2017 ዓ.ም አገልግሎት የሚውል ቋሚ እቃዎች አላቂ እቃዎች ለህጻናት ማቆያ የሚያስፈልጉ እቃዎች የፅህፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት ዕቃዎች፤ የህክምና ዕቃዎች፤ አላቂ ሕክምና እቃዎች፣ መድሃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶት፤ የደንብ ልብስ፣ ዴስክቶፕ እና ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተር፣ ህትመት የሰራተኞች ሰዓት መቆጣጠሪያ ማሽን ከነዝርጋታው የአምቡላንስ ጂፒ ኤስ ከነመግጠሙ ዩፒ ኤስ የመስኮትና በሮች ጥገና የህንጻ ፍሳሽ ማስወገጃ ፒቪሲ ጥገና፣ የሻወር ቤት ጥገና፣ የሎከር ጥግና የመብራት ጥገናና ዝርጋታ፣ የቀለም ቅብ እና የፓርትሽን ስራ የAPTS ሼልፍ ከነ ዴስፕለይ የAshi pit ግንባታ የህክምና እቃዎች ካሊብሬሽን እና የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይንም ግለሰቦች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰቦች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው ሆኖ የዘመኑን ግብር የገበረ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ እና በአቅራቢነት የተመዘገበ ማስረጃ ማቅረብ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የእቃ አይነት ጠቅላላ ዋጋ እና የአንዱን ዋጋ ከፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ በሰጠው ፎርም ላይ መሙላት ይኖርበታል፡፡ የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የነጠላ ዋጋ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን በትክከል በሰም በታሸገ እና ሙሉ አድራሻውን በትከከል በታወቀ ኤንቭሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የእቃዎቹን መስፈርቶች አይነት ሳይለወጡና ሳይነካኩ በተሰጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት (ፎርም) ላይ በትክክል ሞልተው ማቅረብ እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በጤና ጣቢያው ቢሮ ቁጥር 40 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርባቸውን እቃዎች አይነት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- ሲፒኦ (CPO) የሚያያዘው ኮፒው ላይ መሆን አለበት፡፡
- ለጨረታው የቀረበው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በአጋጣሚ ቢሳሳትና ቢስተካከል በቦታው ፊርማ ሊኖረው ይገባል፡፡
- አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት በፍፁም አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን በትከክል በሰም : በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000.00 (ሦስት ሺ ብር) በካሽ (ባንክ ገቢ በማድረግ) የባንከ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ሰዓት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ መለስተኛ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም የጨረታው ሂደት አይሰረዝም፡፡
- መስሪያ ቤቱ አሸናፊው ድርጅት እንደታወቀ የጨረታውን ውጤት ወዲያውኑ ያሳውቃል።
- ማሳሰቢያ፡- ኦርጂናል ፖስታዎች በጨረታ መክፈቻ እና መወዳደሪያ ወቅት የማይከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡- በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ የሚገኝበት ቦታ ቡልጋሪያ አለፍ ብሎ ከኖክ ማደያ በስተግራ ታጥፎ በሚወሰደው መንገድ 150 ሜትር ገባ ብሎ ከሰኒ ሳይድ ት/ቤት ጀርባ ወይም ከኢንተርናሸናል ክሊኒካል ላብራቶሪስ ዝቅ ብሎ ይገኛል፡፡
- ስልክ ቁጥር 011 4 62 49 47
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ
