Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Tourist Trading Enterprise (የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት)
  • Address 22 Mazoriya, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 011-6-61-09-95
  • Websitehttps://www.ette.com.et/
  • Deadline19 Nov 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Installation, Maintenance And Other Engineering Services

ድርጅታችን የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት የባዮሜትሪክ የሰዓት መቆጣጠሪያ ስርዓት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Ethiopian Tourist Trading Enterprise (የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት)


የባዮሜትሪክ የሰዓት መቆጣጠሪያ ስርዓት ግዥ

የጨረታ ቁጥር፡-004/2017

ድርጅታችን የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት የባዮሜትሪክ የሰዓት መቆጣጠሪያ ስርዓት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይነት የምስከር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፤ በጨረታ ተካፋይ ለመሆን መቻላቸውን የሚገልፅ ከሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤና በአፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አቅራቢዎች ድረ-ገፅ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበበት የምስክር ወረቀት ያላቸው።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  3. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ በጨረታው ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት።
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00-6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት ከ7፡30- 11፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የቴክኒካልና የፋይናንሻል ኦሪጂናልና ኮፒ ለየብቻ አሽገው በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በድርጅቱ ግዥ ንብረት አስተዳደርና ቴክኒክ ዳይሬክቶሬት ቢሮ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት በመክተት ይታሸጋል። በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ 22 ማዞሪያ ባቡር መሻገሪያ ቁጥር 1 ፊት ለፊት

በስልክ ቁጥር፦ 011-6-61-09-95/ 011-6-62-24-23

ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

 

የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት

Save Tender