በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስ/ር የአምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል፤ ሎት1 የደንብ ልብስ፤ ሎት2 የመኪና ጎማ፡ ሎት3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4. የጽዳት እቃ : ሎት 5. የህትመት ውጤቶች ሎት 6. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት7 ህንፃ መሳሪያ፣ ሎት 8 ፈርኒቸር፣ ሎት 9 የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ ሎት 10 ደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት11 ተኝቶ ታካሚ ምግብ አቅርቦት በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስ/ር የአምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል፤ ሎት1 የደንብ ልብስ፤ ሎት2 የመኪና ጎማ፡ ሎት3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4. የጽዳት እቃ : ሎት 5. የህትመት ውጤቶች ሎት 6. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት7 ህንፃ መሳሪያ፣ ሎት 8 ፈርኒቸር፣ ሎት 9 የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ ሎት 10 ደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት11 ተኝቶ ታካሚ ምግብ አቅርቦት በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡- የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
- የግዥ መጠኑ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ለሆነ ግዥ በተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያለው::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሡትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 1 በመቶ (1%) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ጥሬ ገንዘብ ከፖስታ በማስገባት ወይም ከሆስፒታሉ ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ ከፖስታው ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- የእቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150 ብር ብቻ ለእያንዳንዱ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ከላይ በሎት የወጡት የጨረታ አይነቶች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ለ15 ቀን በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 ድረስ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ የዙትን ሰነድ አስገብተው 4፡10 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን በሰዓቱ ካልተገኙ ሆስፒታሉ በሌሉበት የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጥንቃቄ ያልታሸገ ፖስታ ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ካላንደር ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊ ተጫራች የአሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አምደወርቅ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብ አለበት ከታዘዘው እስፔስፊኬሽን ውጭ ቢያቀርብ በራሱ ወጭ እቃውን ወስዶ ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት።
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በሆስፒታሉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በቢሮ ስልክ ቁጥር 0334611348 0913805399/0929422992 በመደወል የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
