Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን
  • Address Gurd Shola Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 0929095153
  • Websitehttp://ecwc.gov.et/
  • Deadline05 Nov 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የውሃ ልማት ኮንስትራከሽን ዘርፍ የመገጭ ግድብ ሥራ ፕሮጀከት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የተለያየ አምፔር ያላቸው ባትሪዎች፣ የኬሚካል መያዣ የሆኑ የፕላስቲከ በርሜሎች እና ባዶ የዘይት በርሜሎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የውሃ ልማት ኮንስትራከሽን ዘርፍ የመገጭ ግድብ ሥራ ፕሮጀከት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የተለያየ አምፔር ያላቸው ባትሪዎች፣ የኬሚካል መያዣ የሆኑ የፕላስቲከ በርሜሎች እና ባዶ የዘይት በርሜሎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

  1. ተራጫራቾቹ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የ2016 /2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመገጭ ግድብ ስራ ፕሮጀክት በግዥ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 100 (አንድ መቶ ብር) የኢትዮጵያ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የባንክ አካውንት ቁጥር 1000536733117 (ECWC Head Office Control Account) ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ15/02/2017 ዓ/ም ጀምሮ /10/ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ማዕከላዊ ጎንደር በሚገኘው ፕሮጀክት አዘዞ ከ/ከተማ ጠዳ ወረዳ ቀበሌ ላይ ጠዳ ከአስፓልቱ 2 ኪ.ሜ ገባ ብሎ በፕሮጀክቱ ግዥና አቅርቦት ቡድን ቢሮ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡
  4. አቅራቢዎች የጨረታ ሠነዱን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ 26/2/2017 ዓ.ም እስከ ከሰዓት 11፡00 ድረስ ብቻ ነው::
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋበት በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቶች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ድረስ ለተከታታይ 10 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  8. ፕሮጀክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ተጫራቾች 10% CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ ፡- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጠዳ ከተማ ከሚገኘው 2 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው የፕሮጀክቱ ካምፕ በግዥ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የምትጫረቱበትን የጨረታ ሠነድ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ:- 09-38-35-15-55/09-61-63-45-45

 

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን መገጭ

ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት

Save Tender