Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ ፐልፕ እና ወረቀት አክሲዮን ማህበር
  • Address አ/አበባ ሽሮ ሜዳ አሜሪካን ኢንባስ ፊት ለፊት ቢሮ ቁጥር 33 እና ዋና መስሪያ ቤት ወንጂ ቅጥር ግቢ ውስጥ : ኢትዯጵያ, Phone: 022-220-1793
  • Website
  • Deadline10 Nov 2024, 4:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Security Service

ድርጅታችን የኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት አክስዮን ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት (ለማስጠበቅ) ይፈልጋል።

ኢትዮ ፐልፕ እና ወረቀት አክሲዮን ማህበር


የጥበቃ አገልግሎት ስራ ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን የኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት አክስዮን ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት (ለማስጠበቅ) ይፈልጋል።

የሚጠበቀው የድርጅቱ ሙሉ ቅጥር ግቢ፣ የድርጅቱ የስራ ኃላፊዎች ሚኖሩበት ቅጥር ግቢ እና ስታፍ ከበብ፣የሰራተኞች መኖሪያ ሰፈር ክበብን ጨምሮ፣ ከድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውጪ አዋሽ ወንዝ ዳር የሚገኘውን የድርጅታችን የውሃ ማመንጫ ሞተር እንዲሁም ድርጅቱ ለሰራተኛው በ15 ቀን እና በወር መጨረሻ ለደመወዝ ክፍያ ከባንከ ገንዘብ በሚወጣበት ጊዜ እጀባ በማድረግ ክፍያ እስኪጠናቀቅ ድረስ የድርጅቱን ገንዘብ ካዝና ጥበቃ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ይሆናል።

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላችሁ፡፡
  2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላችሁ፡፡
  3. የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (TIN) ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  4. የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  5. በጨረታ መሳተፍ እንደምትችሉ የሚገልጽ ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  6. የጥበቃ ሥራውን ለማከናወን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ መስራት የሚችል መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  7. በስራው ላይ ከሶስት (3) አመት በላይ ልምድ እና በተጨማሪ የመልካም ስራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ከሰራችሁባቸው ድርጅቶች ተቋም ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  8. ለጥበቃ ሥራው ዕድሜያቸው ከ25-45 ዓመት የሆኑ ሰራተኞች ማሰማራት የምትችሉ፡፡
  9. ለጥበቃ ሥራው የሚሰሩ ሰራተኞች ሙሉ ጤናማ፣ በቂ የአካል ብቃት ያላቸውና በሙያው የሰለጡኑ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  10. ለጥበቃ ሥራው የሚሰማሩ ሰራተኞች ከወንጀል ነፃ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ።
  11. የተደራጀ ቢሮ እና የተሟላ የሰው ኃይል በቋሚነት ያለው፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን CPO ከሚያቀርቡት /ከሚወዳደሩት/ ጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት መቶ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  13. የማወዳደሪያ መስፈርቱ የቴከኒክ ምዘና 70% ፋይናንሻል ምዘና 30% ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ድረስ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ በጨረታ መመሪያ መሰረት በመሙላት የቴክኒከ ማወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒውን የዋጋ (ፋይናንሻል) ማወዳደሪያ ሰነድ አርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች (ኤንቨሎፕ) በማሸግ በተራ ቁጥር 11 በተገለፀው ቀናት ውስጥ ወንጂ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው በግዥና አቅርቦት የሥራ ሂደት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ ከላይ በተገለፀው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያላቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
  15. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የበአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ወንጂ በሚገኘው በድርጅቱ የስራ መሪዎች መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  16. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ወንጂ በሚገኘው የሰው ሃብት ሥራ አመራር ሥራ ሂደት ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 251-022- 22-05-68 በመደወል ማግኘት የሚቻል ሲሆን ከላይ የተገለጸውን ሥራ የሚከናወንበትን ቦታ፣ የግቢውን ስፋት፣ እንዲሁም የጥበቃ ኬላ ብዛት ለማየት የሚፈልግ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በመደበኛ የስራ ሰዓት ወንጂ በሚገኘው በድርጅተ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት ማየት ይቻላል፡፡
  17. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፈል የሚሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት አክስዮን ማህበር

Save Tender