የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2016 ዓ.ም 1. /አንድ/ የገቢ ፋይል እና 2/ ሁለት/ የወጪ ፋይል በጠቅላላው 3. የፋይል አቃፊዎችን ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2016 ዓ.ም 1. /አንድ/ የገቢ ፋይል እና 2/ ሁለት/ የወጪ ፋይል በጠቅላላው 3. የፋይል አቃፊዎችን ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡
የኦዲት ለማድረግ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡-
- ተወዳዳሪዎች የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተወዳዳሪዎች ኦዲት ለማድረግ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የኦዲት ሪፖርቱን በአማርኛና በእንግልዘኛ አዘጋጅቶ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ፣
- ተወዳዳሪዎች የኦዲት ሥራውን ሰርተው ለማጠናቀቅ የሚፈጅባቸውን ጊዜ መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ኦዲት ለማድረግ የተስማሙበትን ዋጋ በግልጽ ይህንን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ 10 ቀናት ጃን ሜዳ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ሣህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከላይ በዝርዝር የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟላ ኦዲተር በዚህ ሥራ ላይ መወዳደር የሚችል መሆኑን እየገለጽን ያልተሟላ መረጃ ለሚያቀርብ ኦዲተር ከውድድር ውጪ እንደሚሆን እያሳወቅን ፌዴሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
