Tender Detail

Tender Details

  • Company የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፓርት ድርጅት
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ኢትዯጵያ, Phone: 011 439 00 75
  • Website
  • Deadline11 Nov 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት የተሽከርካሪዎችን ብልሽት በቀላሉ ለማወቅ የሚያስችል የተሽከርካሪ ብልሽት መመርመሪያ መሳሪያ /Dignostic Scan tools Type 01/ እና /Dignostic Scan tools Type 02/ በዘርፉ ብቃት ያላቸውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፓርት ድርጅት


የተሽከርካሪ ብልሽት መመርመሪያ መሳሪያ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ዕ.ደ.ዕ.ት.ድ/006/2017

ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት የተሽከርካሪዎችን ብልሽት በቀላሉ ለማወቅ የሚያስችል የተሽከርካሪ ብልሽት መመርመሪያ መሳሪያ /Dignostic Scan tools Type 01/ እና /Dignostic Scan tools Type 02/ በዘርፉ ብቃት ያላቸውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት ተጫራቾች፡-

  1. የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) እና ቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ስለመስራታቸው የሚያረጋግጡ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከፋይናንስና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ከዚህ ደብዳቤ ጋር በአባሪነት በቀረበው የሥራ ዝርዝር ላይ የሚወዳደሩበትን ነጠላ ዋጋ (Unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total price) በግልፅ በሚነበብ አሃዝ በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት እስከ ህዳር 02 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በአቅ/ፋ/ማ/ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራች የቴከኒካል ሰነድ ከ70/100 እና የፋይናንሻል ሰነድ ከ30/100 የሚገመገም ለየብቻ እዘጋጅተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የቴክኒካል ግምገማ ውጤት ከ70/100 ወይም 51/70 እና በላይ ያመጡ ተጫራቾች/ ድርጅቶች ለፋይናንሻል ውድድር/ግምገማ ያልፋሉ፡፡ በፋይናንሻል ግምገማ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቹ የሚያቀርበው የነጠላ ዋጋ የመወዳደሪያ ዋጋ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንከ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  9. አሸናፊ ተጫራች ውጤቱ በጽሁፍ እንደተገለፀለት በ7 የሥራ ቀናት ውስጥ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና (ፐርፎርማንስ ቦንድ) ያሸነፈበትን ዋጋ 10% በሲፒኦ በማስያዝ የተዘጋጀውን የስምምነት ውል ይፈርማል፡፡
  10. ጨረታው ህዳር 02 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  11. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 439 00 75/ 011 439 10 27

መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ ነው፡፡

 

የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፓርት ድርጅት

Save Tender