የአብክመ ጤና ቢሮ በመደበኛ በተገኘ በጀት አገልግሎት ላይ የሚውል ሎት1 ዓመታዊ የጽዳት አገልግሎት፤ ሎት2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ሎት3 የወጥ ቤት ዕቃዎች ግዥ ከዚህ በታች በተዘረዘረውና በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ ለመግዛት ይፈልጋል፤
Amhara Health Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ ጤና ቢሮ በመደበኛ በተገኘ በጀት አገልግሎት ላይ የሚውል ሎት1 ዓመታዊ የጽዳት አገልግሎት፤ ሎት2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ሎት3 የወጥ ቤት ዕቃዎች ግዥ ከዚህ በታች በተዘረዘረውና በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ ለመግዛት ይፈልጋል፤ በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መሰረት የሚያቀርቡበትን ዋጋ ሞልተው በመወዳደር አሸናፊ የሆነ ድርጅት ውል በመያዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፊኬት የሚያቀርብ
- ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚገባው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፊኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ ሎት1 ዓመታዊ የጽዳት አገልግሎት ግዥ 70,000.00 /ሰባ ሺህ ብር፣ ሎት2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 200,000.00 / ሁለት መቶ ሺህ ብር፣ ሎት 3 የወጥ ቤት ዕቃዎች 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በባንከ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ የባንከ ዋስትና የሚያስይዙ ።
- ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በታሸገ ፖስታ በጤና ጥበቃ ቢሮ በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ግዥ ከፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 ማስገባት ይችላል። ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን 8:30 ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ከፍል በጃይካ ህንጻ በ16ኛው ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 ታሽጎ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል ።
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ቢሮው የግዥውን መጠን እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 አስራ አምስት ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 200.00 በመክፈል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል ቀርቦ መግዛት ይችላል፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ጤና ቢሮ ግዥ ከፍል ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582221127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃዎች በራሱ ወጭ ክልል ጤና ቢሮ መጋዘን ማቅረብ አለበት ።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት ጤና ቢሮ
