Tender Detail

Tender Details

  • Company Chemical Industry Corporation (ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፓሬሽን)
  • Address Bole, Addis Ababa Ethiopia, Phone: 011-6-62-90-15
  • Websitehttps://www.cic.gov.et/
  • Deadline24 Nov 2024, 2:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Office Machines And Computers

ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለዋና መ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኮምፒዩተሮች፣ ላፕቶፖች፣ ፎቶ ኮፒ ማሽኖች እና ፕሪንተሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Chemical Industry Corporation (ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፓሬሽን)


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኬ.ኢ.ኮ/ግ/ጨ/03-2017

ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለዋና መ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኮምፒዩተሮች፣ ላፕቶፖች፣ ፎቶ ኮፒ ማሽኖች እና ፕሪንተሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን አሟልተው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር አንድ መቶ አምሳ (ብር 150.00) በመክፈል ቦሌ አካባቢ ፍሬንድ ሺፕ ህንፃ ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት አምስተኛ ፎቅ የኦፕሬሽን መምሪያ ቢሮ ቁጥር 05 እየቀረቡ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ሰላሳ (30) ቀናት በአየር ላይ ይውላል፡፡ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ተወዳዳሪዎች ያዘጋጁትን የጨረታ ሠነድ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ኦፕሬሽን መምሪያ ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከሰኞ እስከ ዓርብ ባለው የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ይሆናል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ መወዳደሪያ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዘጋል፡፡
  5. ጨረታው በተዘጋበት ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ 011-6-62-90-15/ 011-6-15-14-68

 

የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፓሬሽን

አዲስ አበባ

Save Tender