የቦሩ ሜዳ ጠ/ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የቀረበውን ዝርዝር በግልፅ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር -ግ/ፋ/ጨ-1/339/2017
የቦሩ ሜዳ ጠ/ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የቀረበውን ዝርዝር በግልፅ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች በቀረበው ሎት ዝርዝር
መሰረት፡-
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የጨረታው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የውድድሩ አይነት |
ምርምር |
|
1 |
ሎት 1 |
ፈርኒቸር /የቢሮ እቃ/ |
20,000 |
በድምር |
ለ 1 ጊዜ ግዥ |
|
2 |
ሎት 2 |
የጥገና እቃዎች |
20,000 |
በነጠላ ዋጋ |
ለ6 ወር የሚቆይ ግዥ |
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለሁሉም ሎት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ (የስራ ፍቃድ) ያላቸው፡፡ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት በሆስፒታል ጊቢ በመቅረብ ከዛሬ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውስጥ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ዋናው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሁሌም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ መጫረቻ ሰነድ ላይ ሲሞሉ ለሁሉም ሎት ቫትን ወይም TOT ጨምሮ መሆን ይኖርበታል፡፡ ለሁሉም ሎቶች የውለታ ማስከበሪያ በመመሪያው መሰረት ውል ይወስዳሉ።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ጋር አብሮ በቀረበው የጨረታ መመሪያ መሰረት ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ንብረቶችን መረካከቢያ ቦታ ሆስፒታል ጊቢ ይሆናል፡፡ እንዲሁም ሆ/ሉ የቫት ሰብሳቢ (ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑን ይወቁ)፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች በሚከፈትበት ቀን ቢኖሩም ባይኖሩም ከመከፈት የሚያስተጓጉል ነገር አይኖርም፡፡
የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም በበዓል ቀን የሚሆን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 033 241 50 05 / ደውለው ይጠይቁን
የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል
