በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ልዩ ዞን የደ/ሀ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለደ/ሀ/ወ/ሴክተር መስሪያ ቤቶች በኩል የሚሰሩ/ የሚገነቡ የተለያዩ ግንባታዎች የሚውል ሎት 1፡- በቱሉ ቦፋ ቀበሌ በደኖ ትምህርት ቤት ግንባታ ሎት 2፡- ግብርና ፑል አጥር ግንባታ ሎት 3፡- ድሬ ቀበሌ ኮሚኒቲንግ ቦንድ (Communiting Bond) ጥገና ስራ ሎት 4፡- ወጨቃ ቀበሌ ግድብ የማስጨረስ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት/ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአሮሚያ ልዩ ዞን የደ/ህ/ወ/ገ/ጽ/ቤት
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ልዩ ዞን የደ/ሀ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለደ/ሀ/ወ/ሴክተር መስሪያ ቤቶች በኩል የሚሰሩ/ የሚገነቡ የተለያዩ ግንባታዎች የሚውል ሎት 1፡- በቱሉ ቦፋ ቀበሌ በደኖ ትምህርት ቤት ግንባታ ሎት 2፡- ግብርና ፑል አጥር ግንባታ ሎት 3፡- ድሬ ቀበሌ ኮሚኒቲንግ ቦንድ (Communiting Bond) ጥገና ስራ ሎት 4፡- ወጨቃ ቀበሌ ግድብ የማስጨረስ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት/ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ፦
- ለስራው በእያንዳንዱ ከላይ በተጠየቀው ዘርፍ/ሎት ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለስራው የምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው፤ ለእያንዳንዱ ሎት የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከሁለት መቶ ሺህ /200 ሺህ /ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላቸው::
- የጨረታውን ሰነድ : ከደ/ሀ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 /ሰባት/ በግዢ/ፋይ/ንብ/ አስ/ዋና የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለሰ የኢትዮጵያ ብር /100/ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በደ/ሀ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሀያ ሁለት /22/ ቀን ከጠዋቱ እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡02 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ በዚህ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተካተቱ ደንብና መመሪያዎች በጨረታ መመሪያው ላይ ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ የጨረታ ሰነድ ሲገዙ ከነ ጨረታ መመሪያ መግዛት ግዴታ ነው።
- ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 ሰላሳ ሺህ ብር (30,000)፣ ለሎት 2- ሰላሳ ሺህ ብር (30,000) )፣ ለሎት 3- ሰላሳ ሺህ ብር (30,000) እና ለሎት 4- ሀያ ሺህ ብር (20,000) በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ መሂ አንድ (1) ገቢ በማድረግ ወይንም በባንክ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ የባንክ ዋስትና /uncondition bank guarantee/ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10%/አስር ፐርሰንት/ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንከ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /uncondition bank guarantee/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አሸናፊው አካል ያሸነፈባቸውን እቃዎች የደ/ሀ/ወ/ገ/ጽ/ ቤት/የጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ያስረክባል፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን እንዲሁም ሙሉ አድራሻቸውን መግለጽ እና ማህተም መምታት አለባቸው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ከ/ደ/ሀ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 0904681980/0911596161/0953047604 /0920405661/0913080626/0913212411/0913641524 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ጨረታው በተመሳሳይ ሰአት በግልጽ ይከፈታል፡፡
በኦሮሚያ ልዩ ዞን የደ/ሀ/ወ/ገ/ጽ/ቤት
