በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል በጋሞ ዞን የሠላምበር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች በ2017 ዓ/ም በመደበኛ በጀት የተለያዩ ማቴሪያሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጋሞ ዞን የሠላም በር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል በጋሞ ዞን የሠላምበር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች በ2017 ዓ/ም በመደበኛ በጀት የተለያዩ ማቴሪያሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚም በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉት
- የህንፃ መሣሪያዎች
- የጽሕፈት መሣሪያዎችና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- የጀነሬተር አይነቶች
- ሞተር ሳይክል አይነቶች
- ስለሆነም በመንግሥት ግዢ አዋጅና ደንብ መመሪያ መሠረት:-
- የታደስ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑ ግብር የተከፈለበት
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር /Tin Number/
- ቫት ተመዝጋቢ የሆነ መረጃ ማያያዝ ይኖርባቸዋል
- ከሽያጭ ዋጋ ላይ የመንግስት ግብር 2% ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የጨረታው ሁኔታ በአይተም /በጥቅል/ ሊሆን ይችላል
- ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በመለየት በአንድ እናት ፖስታ ዉስጥ በማስገባት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በሠ/በር/ከ/አ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ላይ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በጨረታ ሂደት ላይ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ከጠቅላላዉ ዋጋ ላይ የዉል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለበት፡
- ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራአምስት/ ተከታታይ ሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፊል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 / አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በሠላምበር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ይሆናል፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ በቅድሚያ በተዘረዘረው መሰረት የጨረታ ዋስትና የሚሆን ቢያንስ ለ120 ቀናት ፀንቶ ሚቆይ በCPO ወይም ባንክ ጋራንቲ እና ጥሬ ገንዘብ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ከጠቅላላ ዋጋ በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው የጨረታው ማብቂያ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 5፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ15ኛው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- በጨረታ አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ዕቃውን እስከ ሠላምበር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ የጫኚ፣ አውራጅና የጭነት ወጪን በመሸፈን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም የተጫራቹ ወኪል ባለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም፡፡
- በ15ኛው ቀን ሰንበት ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል
ማሳሰቢያ፡ መ/ቤቱ ጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የመ/ቤት ስልክ- 0955325004/0913483495
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የሠላም በር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
