የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለ2017 የበጀት ዓመት ለግዥ የሚያስፈልጋቸው የተለያዩ ዕቃዎች መስፈርቶች ከሚያሟሉ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማኀበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለ2017 የበጀት ዓመት ለግዥ የሚያስፈልጋቸው
ሎት1 አላቂ የጽ/መሣሪያዎች
ሎት2 የጽዳት ዕቃዎች
ሎት3 ፈርኒቸሮች
ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት -
- በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግሥት ግ/ን/አ/ኤ/ድረ ገጽ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ አሸናፊ 10% የጨረታ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ ፤
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ አሥር የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 50/ሀምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎኘ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በግዥ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ታሽጎ በዛኑ ቀን በ10፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሣጥኑ ከመክፈቱ በፊት የተወዳደሩበትን ሎት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ቢሮው ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፤
- አሸናፊ ተጫራች ተወዳድሮ ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው ቢሮ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል፣
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
አድራሻ፡- የደቡብ ኢትዮጰያ ከልል ሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ
የስልክ ቁጥር፡- 046-77-52-968
ጂንካ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማኀበራዊ
ጉዳይ ቢሮ
