የአርሲ በቆጂ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 የበጀት ዓመት በበቆጂ ከተማ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር፤ የማስተማሪያ እቃዎች፤ የስፖርት ልብስ፤ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የአርሲ በቆጂ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-01/2017
የአርሲ በቆጂ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 የበጀት ዓመት በበቆጂ ከተማ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር፤ የማስተማሪያ እቃዎች፤ የስፖርት ልብስ፤ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ፡-
- ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.)፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ እና በፈዴራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የእቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር፣ የማስተማሪያ፤ እቃዎች የስፖርት ልብስ፣ እና የመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በበቆጂ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000041398958 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ፣ ንብረት አስተዳደር፣ ማስወገድና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የፋይናንስ ሃላፊ ቢሮ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር የማስተማሪያ እቃዎች የስፖርት ልብስ፤ እና የመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5.000.00 (አምስት ሺህ ብር)፤ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ በማንኛው ባንከ በክፍያ ማዘዣ (C.P.O.) ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ጥቃቅን እና አነስተኛ ከተደራጁበት ተቋም የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ከምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ በበቆጂ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ ቁጥር 0921082025/0912259200/0913779447 ይጠይቁ።
የአርሲ በቆጂ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
