በአሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የወለጋ ደንና ዱር እንስሳት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በምስራቅ ወለጋ ዲስትሪከት ሥር የሚገኘውን የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር OFWE/BW/Bar.02/2017
በአሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የወለጋ ደንና ዱር እንስሳት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በምስራቅ ወለጋ ዲስትሪከት ሥር የሚገኘውን የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም:-
- የኒንድላ፣ የአጣና፣ የእንጨት መሰንጠቂያ እና ተዛማጅ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች የዘመኑን ግብር የከፈሉና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጊምቢ ከተማ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ወለጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ/የወጣበትን ቀን ጨምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በማግስቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል፡፡
- የቁም ባህርዛፍ ደን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0577711750 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ወለጋ
ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
