በኢትዯጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁትር 1160/2011 መሰረት የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 መሠረት የተተው የተወረሱ ንብረቶቾን ማለትም CAR GLASS POLYESTER YARN, ELECTRIC CABLE & OTHER, OM BASEOIL: MC FLEX SILICONE SANITARYI TRANSFORMER, PVC COVER EXERCISE BOOK & ELECTRIC FORKLIFTI USED OVERLOOK, SEWING & OTHERS MACHINET IRRIGATION PVC FLAT HOSE እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የተተዉ ዕቃዎች ግልፅ ጨረታ ቁጥር ግ-19/2017 ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዯጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁትር 1160/2011 መሰረት የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 መሠረት የተተው የተወረሱ ንብረቶቾን ማለትም CAR GLASS POLYESTER YARN, ELECTRIC CABLE & OTHER, OM BASEOIL: MC FLEX SILICONE SANITARYI TRANSFORMER, PVC COVER EXERCISE BOOK & ELECTRIC FORKLIFTI USED OVERLOOK, SEWING & OTHERS MACHINET IRRIGATION PVC FLAT HOSE እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ መግለጫ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10:30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7:30 እስከ ቀኑ 10:30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5:30 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳቦች በድን መወሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው:: ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅደሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፡ ፡ተጫራቶች የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ከአዲስ አበባ አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት:: ተሳታፊዎች ዋጋ መሙላት የሚችሉት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተዘጋጅቶ ማህተም ያረፈበት ሰነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አስቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፣ በጨረታ ተሸጦ የተወሰደ ዕቃ ተመላሽ አይደረግም፡፡ ለዕቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም፡፡
- የግልፅ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃዎች ለመግዛት በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ በተራ ቁጥር 2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከመጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት እስከ የመጨረሻው ቀን ጠዋት 4፡45 ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል። የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶቹ ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጨምሮ በ8ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
- ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቶች ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፡፡ በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይንም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ጸንቶ ይቆያል፡፡
- የግልጽ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
- በተራ ቁጥር 8 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ያሸነፋበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል ፣ ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል፡፡
- አሸናፊው ተጫራቾች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል፡፡
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፣፣ በጨረታ ተሸጦ በጨረታ አሸናፊው የተወሰደ ዕቃ አይመለስም፡፡
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022-236-9094 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን
የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
