በደቡብ ኢትዮጵያ መንግሥት በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በሎት1. የጽህፈት መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፡ በሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፡ በሎት 3. ለግንባታ አገልግሎት የሚውል የፋብሪካ ውጤቶች ፤ በሎት 4. የሠራተኞች ደንብ ልብስ፤ በሎት 5. የሞተር ሣይክል ፤ በሎት 6. የእንስሳት መድኃኒት እና በሎት 7. የመኪና ጥገና እና የመለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ መንግሥት በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በሎት1. የጽህፈት መሣሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፡ በሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፡ በሎት 3. ለግንባታ አገልግሎት የሚውል የፋብሪካ ውጤቶች ፤ በሎት 4. የሠራተኞች ደንብ ልብስ፤ በሎት 5. የሞተር ሣይክል ፤ በሎት 6. የእንስሳት መድኃኒት እና በሎት 7. የመኪና ጥገና እና የመለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል:-
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደስ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው::
- የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin No/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መረጃ ማቅረብ የሚችል/ትችል፡፡
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/ትችል፡፡
- ለእንስሳት መድኃኒት የኢትዮጵያ የእንስሳት መድኃኒት መኖ አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን የእንስሳት መድኃኒት ድርጅት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አሥራ አምስት/ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ባ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል የጨረታውን ሰነድ እስከ 11፡30 ሰዓት ከገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር-13 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ብር 3000 /ሦስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ "CPO" ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ መሠረት በመሙላት አርጅናል እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ በአንድ ኢንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ማለትም ቅዳሜ፣ እሁድ እና በዓላት ቀናት ሳይጨምር/በዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በ16ኛው የሥራ ቀን 6፡30 ሰዓት ድረስ በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁ.13 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት ወዲያውኑ ታሽጎ በዝያውኑ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡00 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጉ ዕቃዎች መ/ቤቱ ባስቀመጠው ቀን ማቅረብ ግዴታ መሆኑን ማወቅ አለባቸው::
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን፣ ይህም ሲባል ጨረታው በመሠረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም::
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0462420191/096-689-5530 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክ/መንግሥት በጋሞ ዞን ገረሴ
ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
