ከፍተኛ 12 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ/ም ለት/ቤቱ አግልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የከፍተኛ 12 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ከፍተኛ 12 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ/ም ለት/ቤቱ አግልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1/ ሎት 1 የደንብ ልብስ ስፌት 8/ ሎት 8 ማሽነሪ እድሳትና ጥገና
2/ ሎት 2 የደንብ ልብስ 9/ ሎት 9 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
3/ ሎት 3 አለቂ የቢሮ እቃዎች 10/ ሎት 10 ፕላንት ማሽነሪ መግዣ
4/ ሎት 4 ህትመት 11/ ሎት 11 የህንፃ ቁሳቁስ እድሳትና ጥገና
5/ ሎት 5 አላቂ የህክምና እቃዎች 12/ ሎት 12 ለህንፃ ቁሳቁስ ተገጣጣሚ መግዣ
6/ ሎት 6 የትምህርት እቃዎች
7/ ሎት 7 አላቂ የፅዳት እቃዎች
ከላይ ዝርዝራቸው የተጠቀሱ እቃዎች ለማቅረብ የምትፈልጉ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
- የዘመኑ ግብር የከፈለ
- የቫት ከፋይ የሆነ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይና የቲን ቁጥር ማቅረብ የሚችል
- የጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተፃፈ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀን ተጫራቾች የግዥ ሰነዱን ለመግዛት ብር 200 ብር/ ሁለት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል ከት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/ አስተዳደር መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሎቶች ሎት 1፣ ሎት4 ፣ ሎት 5፣ሎት 8 እና ሎት 9 ለየአንዳንዱ ሎት ብር 2000/ ሁለት ሺህ ፤ሎት 2 ሎት 3 ሎት 6 ሎት 7 እና ሎት 10 ለያንዳንዳቸው 5000 ብር/አምስት ሺህ ብር ሲሆን ለሎት 12 3000 ብር/ሦስት ሺህ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ማስረጃ ሲ.ፒ.አ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ተጫራቾች የአሸነፉበትን 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እና ኮፒ በማሸግ አስረኛው የስራ ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛው ቀን ልክ ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ናሙና የሚያስፈልጉት እቃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ /ማሻሻያ /ማድረግ እና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይቻልም፡፡እንዲሁም ከተጠየቀው እስፕስፊኬሽን ውጪ እቃ ማቅረብ አይፈቀድም፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውን ፤ ፊርማቸውን አድራሻቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን ት/ቤቱ ግቢ ድረስ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፈረንሳይ ለጋስዮን ልዩ ስሙ ጉራራ ብረት ድልድይ 12 ቁጥር ፣ 55 ቁጥር እና 64 ቁጥር አውቶቡስ ማዞሪያ ከኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን በስተጀርባ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር :- 011-114-02-96 /011-114-49-86/
011-154-93-31
የከፍተኛ 12 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
