በደቡብ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጉራፈርዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች፣ ላፕቶፕ ኮር አይ7 (Hp Lap Top Core i7) የችሎት አዳራሽ ወንበርና ጠረጴዛ፡ የፋይል መደርደሪያ፣ የቢሮ በር፣ የጋራ አገልግሎት የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ RTR 180 CC ሞተር ሳይክል TVS 150 CC ሞተር ሳይከል፣ የRTR 180 CC ሞተር ሳይክል ጎማ፣ የTVS 150 CC ሞተር ሳይክል ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ፍርድ ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጉራፈርዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች፣ ላፕቶፕ ኮር አይ7 (Hp Lap Top Core i7) የችሎት አዳራሽ ወንበርና ጠረጴዛ፡ የፋይል መደርደሪያ፣ የቢሮ በር፣ የጋራ አገልግሎት የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ RTR 180 CC ሞተር ሳይክል TVS 150 CC ሞተር ሳይከል፣ የRTR 180 CC ሞተር ሳይክል ጎማ፣ የTVS 150 CC ሞተር ሳይክል ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ፡-
- በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሰነድ /Specification/ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት በጉራፈርዳ ወረዳ ፍርድ ቤት የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ቡድን በቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዋጋቸውን ሞልተው የሚያቀርቡት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተቀመጠው የዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎት የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ በሚለው የዕቃዎች ዝርዝር መሠረት ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በወሰዱት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም አርፎበትና ተፈርሞበት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ የዕቃ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ቼክ /CPO/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀን ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ16ተኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- የተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሥነ-ሥርዓቱን አያስተጓጉልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0913986180 /0933215173
በደቡብ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ/ በቤንች ሸኮ ዞን
የጉራፈርዳ ወረዳ ፍርድ ቤት
