በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ኮንስትራክሽን ዘርፍ የዱለቻ አዋሽ አርባ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የተለያዩ አምፔር ያላቸው ባትሪዎች እና ባዶ አስፋልት በርሜሎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን
በድጋሚ የወጣ ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ኮንስትራክሽን ዘርፍ የዱለቻ አዋሽ አርባ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የተለያዩ አምፔር ያላቸው ባትሪዎች እና ባዶ አስፋልት በርሜሎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የ2016 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት በማቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) የኢትዮጵያ ብር ይዘው በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቀን 12/02/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ዱለቻ አዋሽ አርባ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተመለከቱትን መስፈርቶች አሟልቶ ከፍተኛ ዋጋ የሚያቀርበው ተጫራች ሲሆን የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ዱለቻ አዋሽ አርባ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የታሸገ የጨረታ ሠነዱን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ገቢ ማድረግ ይጠበቅባችኋል።
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ከ10 በመቶ /10%/ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።የኢንሹራንስ ቦንድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው ሳጥን መዝጊያ ቀን 28/2/2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ይሆናል።
- የጨረታው ሳጥን መክፈቻ ቀን 28/2/2017 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዱለቻ አዋሽ አርባ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይሆናል፡፡
- ፕሮጀክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-09-29-095153/ 0913860281
በኢ/ኮ/ስ/ኮርፓሬሽን ትራ/መሠ/ል/ኮ/ ዘርፍ የዱለቻ አዋሽ አርባ
መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት
