Tender Detail

Tender Details

  • Deadline01 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Others

የአዲስ አበባ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች በምድብ የተገለጹ ዝርዝሮች በዘርፉ ከተሰማሩ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡


የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  ግ004/2017

የአዲስ አበባ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች በምድብ የተገለጹ ዝርዝሮች በዘርፉ ከተሰማሩ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ምድብ ቁጥር

አገልግልት/የዕቃው ዓይነት

የጨረታ ሰነድ ዋጋ

የጨረታ ማስከበሪያ

 

ምደብ 1

ቦልድ ድንጋይ እና ገረጋንቲ ድንጋይ

300.00

250,000.00 (ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ) በሲፒኦ

ምድብ 2

ኤሌክትሮኒክስ መሰል ዕቃዎች

200.00

30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) በሲፒኦ

ምድብ 3

ለሰርቪስ አገልግልት የሚውል Automatic (Automobile) ተሸከርካሪ እና ሚኒባስ ተሸከርካሪ ኪራይ

200.00

 

30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) በሲፒኦ

ምድብ 4

የአረንጓዴ እጽዋት ዘር እና መጠቅለያ ፕላስቲክ

200.00

 

10,000.00 (አስር ሺህ) በሲፒኦ

 

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምተፈልጉ ተጫራቾች ፡-

  1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የንግድ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ አሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑ ግብር የከፈሉበት ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ድረ-ገጽ (WWW.PPA.gov.et) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ቦለድ ድንጋይ እና ገረጋንቲ ግዥ የምትሳተፉ ተጫራቾች በሕግ አግባብነት ካለው አካል የተሰጠ ለሰብ ቤዝ (የተቆፋሪ ማዕድን) ለማውጣትና ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል የማምረቻ ቦታ ኳሪ እና የባለቤትነት ፍቃድ፣ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ውክልና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጨማሪ መረጃዎች መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው ይሆናል፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በተግለጸው ዋጋ የማይመለስ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ 9ኛ ፎቅ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ከሆነ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሠረት ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታው የሚያቀርቡት ሰነድ ፋይናንሽያል እና ቴከኒካል ለየብቻው ለይተው በፖስታ አሽገው ስም እና አድራሻ በግልፅ በመፃፍ ለዚሁ ለተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት ከቆየ በኋላ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጨራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቴክኒካል ሰነዱ በመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት 10ኛ ፎቅ ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ሕዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡

ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኤጀንሲው አድራሻ ፡-ፒያሳ በተለምዶ እሪ በከንቱ ተብሎ የሚጠራው ቀበሌ 15 ኢትዮ ሴራሚክስ ጎን ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ፊት ለፊት ቢቲ ታዎር (ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር) ነው፡፡

ስልክ ቁጥር - 251-011-275- 0002

የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ

Save Tender