በአብክመ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ በተመደበለት በጀት ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማ፣ ላይነርና ኬርቦይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
የአብክመ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ በተመደበለት በጀት ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማ፣ ላይነርና ኬርቦይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- የአገልግሎት አቅራቢነት ቲን ነምበር ያላቸው፤
- የግዢ መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከ11/2/2017 እስከ 25/2/2017 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ከኮ/ቻ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 የጨረታ ሰነዱን ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ኦሪጅናል ወይም በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታው ውስጥ አስገብተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የእቃ ዝርዝሩን /Specification/ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/ አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 26/2/2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ እለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተጫራቾች ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታ መከፈቻ ጊዜው የበዓል ቀን፣ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይጠበቅብዎታል፡፡
- በጨረታው ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በስልክ ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ለ40 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
- የጨረታው ዉድድር በጠቅላላ ዋጋ ሎት ድምር ነው፡፡
- መምሪያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል
የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 033-3-51-91- 07 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአብክመ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ
