Tender Detail

Tender Details

  • Company Hawassa Industrial Park (ሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ)
  • Address ሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ቅ/ጽ/ቤት የአንድ ማዕከል ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01, Phone: 0462120641
  • Websitehttps://www.ipdc.gov.et/service/parks/9/
  • Deadline29 Oct 2024, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Materials And Raw Materials

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሲገለገልባቸው የቆዩ የተለያዩ የግንባታ ተረፈ ምርቶች (Scrap) እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Hawassa Industrial Park (ሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ)


የሀዋሳ  ኢንዱስትሪ  ፓርክ

ያገለገሉ  ንብረቶች  የሽያጭ  ጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- ሀ/ኢ/ፓ/ሽ/አ/03/2017

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሲገለገልባቸው የቆዩ የተለያዩ የግንባታ ተረፈ ምርቶች (Scrap) እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ግለሰቦች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. በማንኛውም ዘርፍ ህጋዊ የዘመኑን የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታከስ ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው ድርጅት ወይም ማንኛውም ግለሰብ፡፡
  2. የጨረታውን ሰነድ ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ተ.እ.ታ አካቶ በመክፈል ከሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎች መመልከት የሚፈልጉ ከጨረታው መክፈቻ ዕለት አስቀድሞ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ፡፡
  4. ጨረታው ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ላይ በፓርኩ በመገኘት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል፡፡
  5. የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ በታሸገ ፖስታ (Envelope) በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስም የተዘጋጀ ሲፒኦ ወይም ባንከ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  7. አሸናፊ ድርጅት የአሸናፊነት ደብዳቤ በተሰጠው በ 10 ቀናት ውስጥ የንብረቱን ጠቅላላ ዋጋ በመከፈል ንብረቱን ማንሳት ይጠበቅበታል፡፡
  8. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ቅ/ጽ/ቤት የአንድ ማዕከል ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01፣ ስልከ ቁጥር 0462120641

 

የኢንዱስትሪ  ፓርኮች  ልማት  ኮርፖሬሽን

Save Tender