Tender Detail

Tender Details

  • Deadline07 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Others

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 የጨረታ  ማስታወቂያ

ቁጥር 5/2017

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤

  1. የስራተኞች መዝናኛ ክበብ የአገልግሎት ግዥ
  2. የጥበቃ አገልግሎት ግዥ
  3. የቴክኒክ መገልገያ እቃዎች ማሽነሪዎች እና ሌሎች እቃዎች ግዥ
  4. መካከለኛ እና ከባድ ተሽከርካሪዎች ግዥ፣
  5. የቆዳና የጥሬ ዕቃ ማጓጓዣ ኮንቬየር፣ የበሬ ክብደት ማንሻ ማሽን /Chain Hoist/ የሽሆና መቁረጫ ማሽን leg shearer
  6. የመኖ ማሸጊያ ማዳበሪያ፤ የውሻ መኖ ኘላስቲክ ፤ የማዳበሪያ መስፊያ ክር
  7. የጄኔሬተር፣ የላውንደሪ ማሽን እና የበረዶ ቤት የጥገና አገልግሎት፤

ማንኛውም ተጫራች :-

  • በዘርፉ ወይም በተመሳሳይ ህጋዊና የታደስ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያጋግጥ የምስክር ወረቀት ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  • ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በስራ ሰዓት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ማግኘት ይችላል፣
  • የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድቦንድ/ ለሚጫረትበት የጠቅላላ ዋጋውን 2%  በሲ.ፒ.ኦ፣ በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ በድርጅቱ ደረሰኝ ማስያዝይ ይኖርበታል፣
  • የጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሠነዶችን በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣
  • ጨረታው ጥቅምት 28 ቀን 2017ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የጨረታ ኮሚቴዎች ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል::
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-4-65 22 94 /011 4 66 47 05

መጠየቅ ይቻላል::

 

የአዲስ  አበባ  ቄራዎች  ድርጅት

Save Tender