Tender Detail

Tender Details

  • Company የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት
  • Address በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ከብሩክ ህንፃ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113301548
  • Website
  • Deadline04 Nov 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Materials And Raw Materials

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚውሉ ከቦሌ አደባባይ እስከ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ድረስ ያለውን መንገድ በኮሪደር ልማት ለመስራት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ግዥ ለመፈፀም በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ባላቸው አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር-003/2017

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚውሉ ከቦሌ አደባባይ እስከ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ድረስ ያለውን መንገድ በኮሪደር ልማት ለመስራት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ግዥ ለመፈፀም በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ባላቸው አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት-1 የተለያዩ የአካባቢ የግንባታ እቃዎች ሎት-2 የተለያዩ የፋብሪካ የግንባታ እቃዎች

በዚህም መሰረት ፡- ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

    1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
    2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /NAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና ስለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NUMBER/ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
    3. ተጫራቾች በፌዴራል ወይም በክልል የፋይናንስ ቢሮ ወይም በዞን ፋይናንስ መምሪያ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው የእውቅና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
    4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ፣ CPO ሎት-1/50,000 ሎት-2/ 60,000 በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
    5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ማለትም የሚፈልጉትን ጨረታ አይነት (ሎት) የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከወ/ጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ግ/ን/አስ/ዋና/ስራ ሂደት ክፍል ቀርቦ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
    6. ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
    7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ሁለት ኮፒውን በተናጠል ለይቶ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
    8. መ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊ ተወዳዳሪ የሚለየው ተወዳዳሪዎች ባቀረቡት አነስተኛ ዋጋ ወይም በጥቅል ሎት በተሻለውን የጨረታ አሸናፊ የመለየት ስራ ሊስራ ይችላል ።

ማሳሰቢያ ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

በጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡

መ/ቤቱ ከሸጠው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ሞልቶ መወዳደር አይቻልም፡፡

የጨረታ ማስታወቂያውንና የጨረታ ሰነዱ የሚጠይቀውን ዝቅተኛ መስፈርት የማያሟሉ ተጫራቾች ወይም አቅራቢዎች ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ፡፡

የጨረታውን መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ብሄራዊ የህዝብ በዓል ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡

ለበለጠ መረጃ አድራሻ፡- በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ከብሩክ ህንፃ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0113301548/0911921780/ ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡

 

የወልቂጤ  ከተማ  አስተዳደር  ፋይናንስ  ፅ/ቤት

 

Save Tender