በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የህዳሴ ልደታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የስፖርት መምህራን ቱታ፣ ጫማ፣ ፈርኒቸር እቃዎች፣ ኤሌከትሮኒክስ፣ ስቴሽነሪ እና የጽሕፈት መሣሪያ፣ አጋዥ መጽሐፎች፣ ስፌት፣ የፅዳትና ጥበቃ የደንብ ልብስ፣ የመምህራን ጋዎን ጨርቅ፣ ህትመት፣ የአጥር ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀምና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ህዳሴ ልደታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የህዳሴ ልደታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የስፖርት መምህራን ቱታ፣ ጫማ፣ ፈርኒቸር እቃዎች፣ ኤሌከትሮኒክስ፣ ስቴሽነሪ እና የጽሕፈት መሣሪያ፣ አጋዥ መጽሐፎች፣ ስፌት፣ የፅዳትና ጥበቃ የደንብ ልብስ፣ የመምህራን ጋዎን ጨርቅ፣ ህትመት፣ የአጥር ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀምና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም:-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና፣
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ጎማ ቁጠባ ፊት ለፊት ከሚገኘው ህዳሴ ልደታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የዕቃዎቹን ናሙና ማቅረብ የሚችሉ ብቻ የሚወዳደሩ ሲሆን የዕቃ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ሙሉ በሙሉ ጨረታ ላይ የማናወዳድር በሆኑ መቅረብ የማይችሉ ሳምፕሎችን በፎቶ በማቅረብ አድራሻ በመፃፍ ፎቶውን መሰረት በማድረግ ኮሚቴ በአካል መጥቶ የሚያይ ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት /5 የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ባሸነፈበት እቃ ላይ 10% ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በአሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት ባለው በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡00 ሰአት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
- ት/ቤቱ በሚገዛው እቃ ላይ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት 11ኛው ቀን የበዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በቀጣዩ ባለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ካስፈለግዎት በስልክ ቁጥር 0118 698784 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
ህዳሴ ልደታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
