በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አላቂ የፅህፈት መሳሪያ እና የፅዳት እቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልልዊ መንግስት መንግስት የሀዌላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አላቂ የፅህፈት መሳሪያ እና የፅዳት እቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የስራ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያርቡት ዋጋ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ 2% ማስያዝ የሚችሉ፤ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ፤ መልካም የስራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ፤ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ እንዲሁም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ከግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ዋ/የስ ሂደት ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
- አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ወጭ እስከ ቦታው ድረስ ማቅረብ የሚችል።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ለ 20/ሀያ/ ተከታታይ የስራ ቀናት የፅሕፈት መሳሪያ እና የፅዳት እቃ የሚያቀርቡበትን ዋጋ በመግለፅ በፓስታ አሽገው ዘወትር በስራ ሰዓት ሀ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት ግ/ፋን/ን/አስተዳደር የስራ ሂደት ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማኖር ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ21 /ሀያ አንደኛው/ ቀን 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ 5፡30 ሰዓት ይከፈታል። ዕለቱ የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በማግስቱ ይከፈታል።
- ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልልዊ መንግስት መንግስት የሀዌላ
ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት
