በአሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ከተማ የዳበና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለተለያዩ ዲፓርትመንት ማሰልጠኛ እና ለምርት ከፍል የሚውል አላቂና ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የዳበና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ከተማ የዳበና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለተለያዩ ዲፓርትመንት ማሰልጠኛ እና ለምርት ከፍል የሚውል አላቂና ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
- ዕቃዎችን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ከገቢዎች ቢሮ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ 10,000 (አስር ሺ ) በሲፒኦ ማስያዝ የሚችል ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመከፈል በመስሪያ ቤቱ ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋውን የሚገልፅ ዋና እና ኮፒ ፣የቴክኒክ ሰነድ ዋና እና ኮፒ ሆኖ (CPO) ከኦርጅናል ሰነድ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ25/02/2017 ዓ.ም የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ዝርዝር ከምትገዙት ሰነድ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ዕቃውን በ15 ቀን ውስጥ አጠናቀው በደሌ ከተማ ዳበና ኮሌጅ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
አድራሻ - በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ቡኖ በደሴ ዞን በደሴ ከተማ
የዳበና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ስልክ ቁጥር - 047-445-05-75/047-445-04-02
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቡኖ በደሴ ዞን በደሴ ከተማ የዳበና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
