Tender Detail

Tender Details

  • Company የአብክመ በምስ/ጎ/ዞን/አዋበል/ወረዳ/ገ/ኢ/ል/ት/ፅ/ቤት
  • Address ሉማሜ, ኢትዯጵያ, Phone: 0587720630
  • Website
  • Deadline02 Nov 2024, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

በአብክመ በምስ/ጎ/ዞን/አዋበል/ወረዳ/ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴ/መ/ቤቶች ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከመደበኛ እና ከስፖርት ም/ቤት በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የአብክመ በምስ/ጎ/ዞን/አዋበል/ወረዳ/ገ/ኢ/ል/ት/ፅ/ቤት


ግልፅ  የጨረታ  ማስታወቂያ

በአብክመ በምስ/ጎ/ዞን/አዋበል/ወረዳ/ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴ/መ/ቤቶች ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከመደበኛ እና ከስፖርት ም/ቤት በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት1. የጽህፈት መሳሪያ ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች፣ ሎት 2. የመምህራን የእስፖርት አልባሳትና ጫማዎች፣ ሎት 3. የእስፖርት እቃዎችና መገልገያዎች፣ ሎት 4. ጫማና የቆዳ ውጤቶችና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 5. የመኪና ጎማ ከነመሰል ካላማንዳሪው፣ ሎት 6.የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ ሎት 7. ብትን ጨርቅና የተዘጋጁ አልባሳት፣ ሎት 8 የመኪና ጥገና፤ ሎት 9. የስፖርት ምከር ቤት የስፖርት አልባሳትና ጫማዎች፤ ሎት 10. ክሎሪን ፤ ሎት 11. የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች፤ ሎት 12. ህትመት እና ተዛማጅ ስራዎች፤ ሎት 13. የውጭ ፈርኒቸር፣ ሎት 14. የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር፣ ሎት 15. ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች፤ ሎት 16. የቤት እና የቢሮ አቃዎች መገልገያዎች እና ማስዋቢያዎች፤ ሎት 17. የንፅህና መጠበቂያ እና የኮስሞቲከስ ዕቃዎች፣ ሎት 18. የእስካቫተር ኪራይ፤ ሎት 19. የመለኪያ እና የመፈተሻ መሳሪያዎች፤ ሎት 20. የኤሌክትሪክ እቃዎችና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈትሮች የሚያሟላ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው::
  3. የጨረታ ተሳታፊዎች የሚሞሉት ዋጋ ከ200.000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት/VAT/ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  5. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ/እስፔስፍኬሽን ከእያንዳንዱ ሎት /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የመሸጫ ዋጋ 30 /ሰላሳ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት1 ፣ ሎት2፣ ሎት4፣ ሎት6፤ ሎት 7፤ ሎት8 ፤ ሎት 12፤ ሎት 15 እና ሎት18 ብር 15.000 እንዲሁም ሎት5፤ ሎት3፤ ሎት9፤ ሎት 13 እና ሎት14 ብር 10,000 እና ሎት 10፤ ሎት 12፣ ሎት 16፤ ሎት 17፤ ሎት 18፤ ሎት 19 እና ሎት 20 ብር 5.000 በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በመሂ አንድ ማስያዝ አለባቸው::
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም እንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች እና ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በወጣው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ በጽ/ቤቱ በግዥ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት አስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በ16ኛው ቀን እስከ 3፡30 ማስገባት የሚቻል ሲሆን በ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0587720630/0004 በመደወል ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው ሲከፈትም ሆነ ከተከፈተ በኋላ የሚገኝ ከጥቃቅን ስህተቶች በስተቀር ከባድ ስህተቶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
  12. መ/ቤቱ ጨረታውን 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው::
  13. የእቃውን ዋጋ የሚሞላው ከጨረታው ጋር በምናቀርበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ሆኖ እስፔስፊኬሽን ቀይሮ መሙላት የተከለከለ ነው፡፡.
  14. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  15. አሸናፊው ያሸነፋቸውን እቃዎችን አዋ/ወ/ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት ድረስ ያለማንጠባጠብ አጠቃሎ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  16. አሸናፊው በሎት ይለያል በሎቱ ውስጥ የተጠቀሱት ዝርዝሮች በሙሉ ዋጋቸው መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡
  17. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙናውን አዋ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በግዥ ቢሮ ቁጥር 06 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  18. ማንኛውም የሚቀርበው እቃ ኦርጅናል መሆን አለበት፡
  19. የመኪና ጥገና አገልገሎት፤ የመኪና መለዋወጫ እቃ፤ ጎማ ከነመሰል ካላማዳሪ እና ህትመት አሸናፊ የሆነ አካል ወይም ድርጅት አገልግሎቱን ወይም ግዥውን በውሉ መሰረት እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ./ም ድረስ ማቅረብ ወይም መፈፀም አለበት፡፡
  20. አሸናፊ የሆነው አካል ድርጅት ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ ከ40 ቀናት በፊት እቃውን ማቅረብ አለበት።

በአብክመ በምስ/ጎ/ዞን/አዋበል/ወረዳ/ገ/ኢ/ል/ት/ፅ/ቤት

ሉማሜ

Save Tender