የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በባህር ዳር ሪፈራል ሆስፒታል (13-04B) ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Redash በራሳቸው ትራንስፖርት ብዛት 800 m3 ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በባህር ዳር ሪፈራል ሆስፒታል (13-04B) ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Redash በራሳቸው ትራንስፖርት ብዛት 800 m3 ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት
|
የፕሮጀክቱ ስም
|
የጨረታ ቁጥር
|
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ
|
|
1 |
Redash
|
ሪፈራል ሆስፒታል (13-04B) ፕሮጀክት
|
DCE/13-4B/068/2024
|
ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል |
ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ይከፈታል |
50,000.00
|
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሠማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀትና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታክስ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ. ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ለ60 (ስልሳ) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በፕሮጀክቱ በሚገኝበት ወራሚት ቀበሌ በሚገኘው ሪፈራል ሆስፒታል ግዥና አቅርቦት ቡድን ቢሮ መግዛት ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በሰንጠረዥ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ባህር ዳር ሪፈራል ሆስፒታል ፕሮጀክት ወራሚት ቀበሌ ወደ መኮድ ም/ዕዝ መታጠፊያ መንገድ 500 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር 09 31 863 257/09 18 446 278 ይደውሉ፡፡
መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
