በሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ፅ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን እና የተለያዩ አዳዲስ የመኪና መለዋወጫዎችን እና የሕንፃ መስሪያዎችን ያሉ ጄኔሬተሮችን እና ሌሎች ያገለገሉ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አውዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ፅ/ቤት
በሽያጭ መለያ ቁጥር ሐረ-ተሸ ሸያጭ 001/2017 የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን እና
በሽያጭ መለያ ቁጥር ሐረ-ንብ ሽያጭ 002/2017 የተለያዩ አዳዲስ የመኪና መለዋወጫዎችን እና ሕንፃ መስሪያዎችን ያሉ ጄኔሬተሮችን እና ሌሎች ያገለገሉ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ፤
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ በመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ ጽ/ቤቱ ለሽያጭ መለያ ቁጥር ሐረ-ን. ሽያጭ/01/2017 ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) እና የሽያጭ መለያ ቁጥር ሐረ-ተሸ ሽያጭ 002/2017 ብር 200 በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ዘውትር በስራ ሰዓት በጨረታ ዶክመንት ውስጥ በተጠቀሰው መስሪያ ቤት ድረስ በመሄድ የሚወዳደሩባቸውን ንብረቶች እና ተሽከርካሪዎች መመልከት ይቻላል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ንብረቶች ጠቅላላ ዋጋ በመነሻ ዋጋ 10% እና ለተሽከርካሪዎች 20% ጠቅላላ መነሻ ዋጋ የሚሆነውን ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሚቀርቡት ጨረታ ሰነድ ጋር ለመያያዝ እና በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው CPO በሐረሪ ህዝብ ከልላዊ መንግስት በመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገለግሎት ሰጪ ፅ/ቤት ስም መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ሲያቀርቡ በታሸገ ፖስታ ሆኖ በፖስታው ላይ የተጫራቾች ሙሉ ስም ፤ፊርማ ፤እና አድራሻ በማይለቅ ቀለም በመፃፋ ማቅረብ ይኖርባቸል።
- ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚጠበቅባችው ማስረጃዎች እድሜ 18 አመት እና ከዚያ በላይ መሆኑን እና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- የሽያጭ መለያ ቁጥር ሐረ-ተሸ.ሽያጭ 001/2017 ጥቅምት 20/2017 ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ፅ/ቤት ይከፈታል።
- የሽያጭ መለያ ቁጥር ሐረ-ንብ.ሽያጭ 002/2017 ጥቅምት 21/2017 ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወያም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልገሎት ሰጪ ፅ/ቤት ይከፈታል።
- የጨረታው አሽናፊ ያሽነፈባቸውን ተሽከርካሪዎች እና ንብረቶች የሸያጭ ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ጠቅላላ ክፍያ በመፈፀም ማንሳት የኖርበታል።
- ተጫራቾች ያሸነፋትን ንብረት እና ተሽከርካሪዎች በሚያነሱበት ወቅት የማጓጓዣ ከፊያዎች በራሳቸው የሚሸፈን ይሆናል።
- የበለጠ ለመረዳት በስልክ ቁጥር 09 20 01 62 96 በመደወል ማነጋገር ይቻላል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለማብራሪያ እና ጥያቄ የሻጭ አድራሻ የጽ ቤቱን ድረ ገፅ www.HPPDSO.GOV.ET ቴሌግራም http://t.me/Hppdso
- ስልክ 092 001 696 አድራሻ ተረር አራተኛ አደባባይ 100 ሜት ወረድ ብሎ በሚገኘው ዘቢዳ ህንፃ 4ኛ ወለል ላይ ነው።
በሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና
ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ፅ/ቤት
