Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913247806
  • Website
  • Deadline30 Oct 2024, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለመቀግ/ወ/ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ ከሕጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለመቀግ/ወ/ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመደበኛ በጀት 1ኛ. የፅህፈት መሳሪያ፣ 2ኛ. የደንብ ልብስ ያልተዘጋጁ ብትን ጨርቆች፤ የተዘጋጁ ጫማዎችና የተዘጋጁ ልብሶች፣ 3ኛ. የፅዳት እቃ፣ 4ኛ.ልዩ ልዩ እቃዎች፣ 5ኛ ህትመት ስራ፤ 6ኛ, ቋሚ እቃ ኤሌከትሮኒከስና ወንበር ጠረጴዛ፣ 7ኛ. የግንባታ እቃ፣ 8ኛ, የመኪና መለዋወጫ እቃ፤ 9ኛ. የቢሮ ማስዋቢያና ማስጌጫ ምንጣፍ 10ኛ. በስፖርት ምክር ቤት በጀት የስፖርት ትጥቅና የስፖርት እቃዎች 11ኛ በሴፍቲኔት በጀት የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ከሕጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል ፡፡ በመሆኑም በአንድ ሎት/ምድብ/ ያሉት እቃዎች ዋጋቸው ከ200,000/ ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ የሆኑ እቃዎች ላይ መወዳደር የሚችሉት የቫት ተመዝጋቢ የንግድ ድርጅቶች ብቻ ሲሆኑ ከብር 200.000/ ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በታች የሆኑት እቃዎች ላይ መወዳደር የሚችሉት የቫት ተመዝጋቢ የሆኑም ያልሆኑም ድርጅቶች ይሆናሉ፡፡ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ፣ አግባብነት ያለው የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) እና የቫት ተመዝጋቢ ማረጋገጫ ማስረጃ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመደበኛ በጀት ለተከታታይ 15 ቀናት ለሴፍቲኔት በጀት ተከታታይ 30 ቀናት ሲሆን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በ200 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት የሚያቀርቡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ መሰረት በመሙላት አንድ ኦርጅናል በማሸግ በመ/ቀ/ገ/ወ/ገ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ 1. ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ መሰረት መሙላት አለባቸው።

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% ብር ከነቫቱ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  2. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለመደበኛ በጀት 15 ተከታታይ ቀን ሲሆን በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል እና ለሴፍቲኔት በጀት 30 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ31ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል 16ኛው እና 31ኛው ቀን የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል ::
  3. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዋጋ ዝርዝር ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ፣ በፍሉድ የተሰረዘ ወይም ለማንበብ አስቸጋሪ የሆነ ሰነድ የተከለከለና ከጨረታ የሚያሰርዝ ይሆናል፡፡
  4. ለጨረታ የሚያስፈልገውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ያላቀረቡ ተጫራቾች በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት ከጨረታ ውጪ ይደረጋሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ እና ፖስታው ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ መሆን አለበት።
  7. የጨረታ ስርዓቱን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያቸውን በመውረስ ወዲያውኑ ከጨረታ ውጪ ይደረጋሉ፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ በኋላ የሚያቀርቡት እቃ በጨረታ ሰነድ ስፔስፊኬሽን መሰረት ኦሪጅናል እቃ ማቅረብ አለባቸው ::
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ናሙናን በተመለከተ ፅ/ቤቱ የፕሪንተር ወረቀት ፣የፕሪንተር ቀለም ፣ የደንብ ልብስና የስፖርት ትጥቅ ፅ/ቤቱ ስለሚያቀርብ ከናሙናው ያነሰ እቃ የማንቀበል ሲሆን ተወዳዳሪዎች ናሙናውን በማየት ዋጋ መሙላት አለባቸው ሌሎቹን እቃዎች አንደኛ ደረጃ ኦርጂናል እቃ መቅረብ አለበት ::

የመንዝ ቀያ ገብረኤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን

ስ.ቁ 0913247806/0921747797

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ

ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት

Save Tender