Tender Detail

Tender Details

  • Company ጋፋት ኢንዶውመንት
  • Address Bahir Dar Ethiopia, Phone: 0582266147
  • Websitehttp://gafatendowment.org/
  • Deadline23 Oct 2024, 4:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Others

ጋፋት ኢንዶውመንት በኢንዶውመንቱ ስም ፕሮጀክት ቀርፀውና ከለጋሽ ስካላት ግራንት አፈላልገው ሃብት ሊያመጡ የሚችሉ ህጋዊ ድርጅቶች/ባለሙያዎችን ከሚያመጣው ሃብት ላይ በፐርሰንት ኮሚሽን በማሰብ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ጋፋት ኢንዶውመንት


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ

የጨረታ ማስታወቂያ

ጋፋት ኢንዶውመንት በክልሉ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ማህበራት መመዝገቢያና ማስተዳደሪያ አዋጅ ቁጥር 194/2004 አንቀጽ 63(1) መሠረት የተመዘገበ መንግስታዊ ያልሆነ ዘላቂ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡

ስለሆነም “በኢንዶውመንቱ ስም ፕሮጀክት ቀርፀውና ከለጋሽ ስካላት ግራንት አፈላልገው ሃብት ሊያመጡ የሚችሉ ህጋዊ ድርጅቶች/ባለሙያዎችን ከሚያመጣው ሃብት ላይ በፐርሰንት ኮሚሽን በማሰብ” አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች ግለሰቦች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤

  1. የታደሠ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ምስክር ወረቀት ሊያቀርቡ የሚችሉ፣
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ቀን በ10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ በ10፡30 ሰዓት በኢንዶውመንቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 20 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ ህግ የተጠበቀ ነው።
  7. ለተጨማሪ መረጃ አድራሻችን፣ ጋፋት ኢንዶውመንት

ስልክ ቁጥር፡- 0582266147/0583207679

 

ባህር ዳር ጋፋት ኢንዶውመንት

Save Tender